መነሻ ገጽ መቐለ ከተማ ሪፖርት | ደደቢት በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ድሉን መቐለ ከተማ ላይ ተቀዳጅቷል
መቐለ ከተማሪፖርትደደቢት

ሪፖርት | ደደቢት በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ድሉን መቐለ ከተማ ላይ ተቀዳጅቷል

አጋራ
አጋራ


በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል ተጠባቂ የነበረው መቐለ ከተማ ደደቢትን አስተናግዶ 2-0 በሆነ ውጤት በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ሊሸነፍ ችሏል

ከጨዋታው አስቀድሞ ሁለቱም ቡድኖች በመቐለ ዩኒቨርስቲ ትልቅ ባስ ታጅበው በሕብረት ነበር ወደ ሜዳ መግባት የቻሉት፡፡ ሁለቱም ክለቦች ወደ ሜዳ ሲገቡ ከመቐለ ከተማ ደጋፊዎች ሞቅ ያለ አቀባበል ሲደረግላቸው ቀድመው ወደ መልበሻ ክፍል የገቡት መቐለ ከተማዎች (አየኩም ናይና) =>አየዟችሁ የኛዎቹ በሚለው ዜማ ታጅበው ሲገቡ በአንጻሩ ተጋጣሚቸውን ደደቢት ደደቢት በሚለው ድምፅ ከዳር እስከዳር ያለ ደጋፊ በአንድ ድምፅ ድጋፍ ሲቸራቸው የ ደደቢት ተጫዋቾች የክለቡን መለያቸውን እያወለቁ ወደ ደጋፊው ሂደው ሲወረዎሩት ድምፁ ከፍ ብሎ ከባለሜዳዎ ክለብ በላይ ተደምጠዋል፡፡ ከዚ በኃላ ነበር መቐለ ከተማ ተጫዋቾች ጥቁር ሪቫን አስረው ከመልበሻ ክፍል ሲወጡ ፥ ደደቢቶች ደግሞ ጥቁር ማልያ ከላይ ለብሰው ማልያው say no to Racism የሚል ፅሑፍ ያለውን ጽሁፍ በማድረግ ወደሜዳ በመግባት የ1 ደቂቃ የሕሊና ፀሎት በማድረግ ነበር ወደ ጨዋታው ያመሩት፡፡

የሁለቱ ቡደኖች ጨዋታ አንደ ተጀመረ በ 4-5-1 በሆነ ቅርፅ አሰላለፍ ይዘው የገቡት መቐለ ከተማዎች ሲሆኑ በተመሳሳይ 4-5-1 አሰላለፍ በመያዝ ተጋጠሚያቸው ሰማያዊ ለባሾቹ ደደቢቶች ይዘው መግባት ችለዋል፡፡ ከመጀመርያው የዳኛ ፊሽካ መነፋት ጀምሮ በደደቢት ጨዋታ የተበለጡ ይመስሉ ነበር
መቐለዎች ከእረፍት በፊት ከጨዋታ ውጪ አቀቋም የነበረው 55ቁጥሩ ፒስማርክ አግብቶት ከተሻረችው ኳስ በስተቀር የሄነው የሚባል ኳስ በሁለቱ በኩል አልተመለከትንም፡፡ በሙከራ ያልታጀበና ደጋፊውን ያላዝናና ሙከራ ያልታይበት ጨዋታ ነበር፡፡
ከእረፍት በፊት መድሃንኔ ታደሰና አሞስ የሞከሩት ቀለል ያሉ ኳሶች ለግብ የቀረቡ ሙከራ ተብለው ሲጠቀሱ ፣ በ 27ኛ ደቂቃና በ 41 ኛ ደቂቃ ሁለት የመአዝን ምት በመጀመሪያው አጋማሽ ያገኙት
ደደቢቶች ከመቐለዎች የተሻለ የኳስ ቅብብልና ኳስ አደራጅተው ለአጥቂያቸው ጌታነህ ከበደ ኳስ በማድረስና በኳስ ቁጥጥር እና ፖሴሽን ደደቢቶች በመጀመርያ 45 ከመቐለዎች ልቀው የተገኙ ሲሆኑ ከእረፍት በፊት በ 42ኛ ደቂቃ ከኤፍሬም አሻሞ የተላከለትን የመስመር ኳስ ጌታነ ከበደ ወደ ግብ ቀይሮ በደደቢት 1-0 መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
ከእረፍት መልስ መቐለዎች ዱላ ሙላቱን ቀይረው በማስገባት ወደ ሜዳ የተመለሱት መቐለዎቹ በ 48 ኛ ደቂቃ አመለ ሚልኪያስ በግምት 20 ሜትር አካባቢ አክርሮ የመታው ቅጣት ምት ኳስ ፊሊፕ ኦቦኖ የመለሰው ሲሆን በ 53 ደቂቃ በእለቱ ጥሩ ያልነበረውና ከጉዳት ተመልሶ ወደ ቋሚ አሰላለፍ የገባ ፒስማርክ አቅጣጫውን ያልጠበቀ ሙከራ በደጋፊው  ተቃውሞ እንዲነሳበት አድርጓል ፡፡ በተከታታይ በ 59 ደቂቃ የቀዮቹ  10 ቁጥር ለባሽ ያሬድ ከበደ   ከ25 ሜትር አኽርሮ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ  የጎሉን ብረት   ተጠግታ የወጣችው  ኳስ መለች በ 90ደቂቃ ውስጥ ከሞከሯቸው ኳሷች ለጎል የቀረበች  ነበር::

በ 65ኛ ደቂቃ   ተቀይሮ የገባው ዱላ ሙላቱ   በፍፁም ቅጣት ክልል ውስጥ በተሰራ ጥፋተ የእለቱ ዳኛ   ለመቐለ ከተማ የፍፁም ቅጣት ምት የሰጡ ሲሆኑ  መድሃኔ  ታደሰ   ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
  በ 72  ደቂቃ ላይ  አቤል እንዳለን   ተክቶ የገባው    አለም አንተ  ካሳ (ማርዮ) በ 83 ደቂቃ  ከጌታነህ ከበደ  የተላከለትን ኳስ  ወደ  ግብነት በመቀየር     የክለቡ  የ1ለ0 መሪነት  ወደ 2-0 አሳድጎ   ለሰማያዊ ለባሾቹ  እፎይታ ሲፈጥር  ለ ቀይና ነጭ ለባሾቹ መቐለ ከተማዎች  ተስፋ ያስቆረጠች  ግብ ነበረች፡፡   በ 85 ደቂቃ  መቐለዎች  በእለቱ ጥሩ  ያልነበረውን  ፒስማርክ ን አስወጥተው   ዳዊት ዑቅባዝጊ  ቀይርው ያስገቡ  ሲሆን በአንጻሩ    መሪዎች ደደቢቶች ኤፍሬም አሻሞ በማስወጣት ሄኖክ መርሹን   አስገብተው  ውጤታቸውን አስጠብቀው ወጥተዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሪፖርትቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማወልቂጤ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማና ወልቂጤ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

በሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ሶስተኛ ጨዋታ የተገናኙት አዳማ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ በአንድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግየዝውውር ዜናዎችደደቢት

ብሩክ ገብረአብ ለደደቢት ፈርሟል !

  ከሳምንት በፊት ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲን እንደተቀላቀለ የተገለፀው ብሩክ ገብረአብ ከቡድኑ ጋር...

ዜናዎችደደቢት

ደደቢት በፌደሬሽኑ ታገደ

  ደደቢት የብርሀኑ ቦጋለ ደሞዝ ባለመክፈሉ ምክንያት ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ታግዷል። ደደቢት...