በናሁሰናይ ታምር
በ6 ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀግብር አርባምንጭ ከተማ ከ ውልዋሎ.ዓ.ዩ ያገናኝው ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታው መጠናቀቅያ አከባቢ በሁለቱም ብድኖች በተቆጠሩ ግቦች 1-1 የአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
አርባምንጭ ከተማ መከላከያ ላይ ይዞ ከገባው አሰላለፍ የ1 ተጫዋች ለውጥ በማድረግ ታድዮስ ወልዴን በአለልኝ አዘነ በመቀየር ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን፡፡
ውልዋሎ በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ይዞ የገባውን አሰላለፍ በዚህም ጨዋታ ላይ መተግበር ችሏል፡፡
ሁለቱም ኳስን መሠረት አድርገው ሚጫወቱ ቡድኖች እደመሆናቸው መጠን በመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም መሀል ክፍል ተጫዋቾች ኳስን በልጦ ለመጫወት ጫናወችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ተስተውሏል፡፡
ከዚህም ባለፈ አንድ-ሁለት ጊዜ በአርባምንጭ በኩል ብርሀኑ አዳሙ በውልዋሎ በኩል ፕሪንስ ሰቨሪኒሆ በመሰመር የተቃራኒ ተጫዋቾችን በማለፍ ወደ ግብ ለመድረስ ሲሞክሩ፡፡በ38 ደቂቃ ፕሪንስ ሰቨሪኒሆ ያሻማውን ኳስ ሙልአለም ጥላሁን ወደ ግብ የመታው የጎሉን አግዳሚ ብረት በመግጨት ወደ ዉጭ የወጣበት ኳስ ውልዋሎ መምራት የሚያስችልበትን ዕድል ነበረች፡፡
ከዚህ ውጪ በሁለቱም በኩል የረባ እንቅስቃሴ ሳይደረግ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው አጋማሽ ባለሜዳወቹ አዞዎቹ በፍፁም የበላይነት ጨዋታውን መቆጣጠር ሲችሉ::
በተለይም በአጥቁወቹ ብርሀኑ አዳሙ አና ላኪ ሳኒ አማካኝነት ሁለት ያለቀላቸውን ኳሶች አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡
በተለይም በ70’ደቂቃ ታዳጊው አጥቂ ብርሀኑ አዳሙ የግል ብቃቱን በመጠቀም ከመሀል ሜዳ ይዞ የወጣውን ኳስ የውልዋሎ ተጫዋቾችን በማዘናጋት ወደ ግብ ደርሶ ወደ ውጪ ያወጣው ኳስ ለአዞዎቹ መሪ የሚሆኑበትን ዕድል ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡
በብዙ የዳኝነት ስህተት ውዝግብ ና በውልዋሎ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ መውደቅ የቀጠለው ጨዋታ በ83 ደቂቃ ውልዋሎዎች በአንድ-ሁለት ተቀባብለው ተቀይሮ በገባው ወግደረስ ታዬ አማካኝነት መሪ መሆን ሲችሉ፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በሃላ በ86ደቂቃ በውልዋሎ ተከላካይ አማካኝነት በእጅ በመነካቱ ዳኛው ፍፁም ቅጣት ምት የሰጡትን ኳስ ላኪ ሳኒ ወደ ግብ በመቀየር አዞዎቹን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡
ከጎሉ መቆጠር በሃላ አዞዎቹ ወደ ግብ መድረስ ቢችሉም ጎል ማስቆጠር ተስኗቸው ጨዋታው በ1-1 አቻ ውጤት ልጠናቀቅ ችሏል፡