መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል
ሲዳማ ቡናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል

አጋራ
አጋራ

 

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ዕለት ጨዋታ ቀን 10:00 ሰዓት ሲል የተገናኙት ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን አንድ አቻ በሆነ ዉጤት አጠናቀዋል።

ወልቂጤ ከተማዎች ከቀናት በፊት በ27ኛዉ ሳምንት ጨዋታ በፈረሰኞች ከተረቱበት ጨዋታ የአራት ተጫዋቾችን ለዉጥ አድርገው ወደ ሜዳ ሲገቡ በአንፃሩ ሲዳማ ቡናዎች መኳንንት ካሳን በጊት ጋት ኮት ብቻ ቀይረዉ ወደ ሜዳ ገብተዋል።

የጨዋታውን የመጀመሪያ ደቂቃዎች በጥሩ እንቅስቃሴ የጀመሩት ሲዳማ ቡናዎች ገና በ5ኛዉ ደቂቃ ላይ እጅግ ለግብ የቀረበን ሙከራ ማድረግ ችለዋል። በተጠቀሰዉ ደቂቃ ከግብ ጠባቂዉ ሮበርት ኦዶንካራ የተመለሰዉን ኳስ አጥቂዉ ሳልሃዲን ሰይድ አግኝቶ ለዳዊት ተፈራ ቢያቀብለዉም ተጫዋቹ ኳሷን ወደ ግብ መቀየር ሳይችል ቀርቷል።

ከዚች የጨዋታው የመጀመሪያ ሙከራ በኋላ ደግሞ ወልቂጤ ከተማዎች በቶሎ ድንቅ የሚባል ሙከራን ማድረግ ችለዋል። የወልቂጤ ከተማዉ የአጥቂ መስመር ተጫዋች አቡበከር ሳኒ ከቀኝ መስመር አክርሮ ወደ ግብ የላካት ኳስ በግብ ዘቡ መክብብ ደገፋ ከሸፈች እንጅ ምናልባትም ክቶፎዎቹ መሪ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ነበር።

በ18ኛዉ ደቂቃ ላይ ግን በዕለቱ ጥሩ ጥሩ ሊባሉ የሚችሉ በርካታ ሙከራዎች ሲያደርግ የነበረዉ አጥቂው ሳልሃዲን ሰይድ ሲዳማ ቡናን መሪ ማድረግ ችሏል። ከቀኝ መስመር በኩል ከአማኑኤል የተሻገረለትን ኳስ ሰልሀዲን ሰይድ ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

ከግቧ መቆጠር በኋላ ክትፎዎቹ በእነ ዮናታን ፍስሀ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ እና አቡበከር ሳኒ አማካኝነት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ የመጀሪያዉ አጋማሽ በሲዳማ ቡና 1ለ0 መሪነት ተገባዷል።

ከዕረፍት መልስ በተደጋጋሚ ተጭነዉ በመጫወት የአቻነት ግብ ለማግኘት ሲታትሩ የነበሩት ክትፎዎቹ ዉጥናቸዉ ሰምሮ አቻ መሆን የቻሉበትን ግብ በ58ኛዉ ደቂቃ ላይ አስቆጥረዋል። በሲዳማ ቡናዎች የግብ ክልል ዉስጥ ጫላ ተሽታ ላይ ጥፋት መሰራቱን ተከትሎ የተገኘዉን ፍፁም ቅጣት ምት ሀብታሙ ሸዋለም ወደ ግብነት ቀይሮ ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል።

 

ወልቂጤ ከተማዎች የአቻነቷን ግብ ካስቆጠሩ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች በኩል እንደመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ፋክክር አይተንበታል ባይባልም ሲዳማ ቡናዎች በተለይ ጨዋታው ወደ መገባደጃዉ ሲቃረብ የተወሰኑ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ ነበር በተለይ አማካዩ ሙሉአለም ከማዕዘን የተሻገረዉን ኳስ ቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክርም የግብ አግዳሚዉ የመለሰበት አጋጣሚ በሲዳማዎች በኩል በጨዋታው መገባደጃ ወቅት የተገኘ አስቆጭ እድል ነበር። በመጨረሻም የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በዚህ ሂደት አምሮቶ አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።

በቀጣይ ሲዳማ ቡና ከአዲስአበባ ከተማ ጋር ሲገናኙ በአንፃሩ ወልቂጤ ከተማዎች ደግሞ ከጅማ አባጅፋር ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...