ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ ተወሰነ።

በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ለሁለት ክለቦች በመፈረማቸው መነጋጋሪያ ርዕሰ ሆነው የቆዩት አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ እና የመስመር ተከላካዩ አለምብርሀን ይግዛዉ አሁን ላይ ጉዳያቸዉ የመጨረሻ ዕልባት አግኝቷል።
ሁለቱ ክለቦች ባደረጉት ስምምነት መሰረት አለም ብርሀን ይግዛዉ ለመቻል እንዲጫወት ሲስማሙ አብዱል ከሪም ወርቁ ደግሞ ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወት እንደተወሰነ ታውቋል።
የመቻሉ የመስመር ተከላካይ አለምብርሀን ይግዛዉ ነገ ክለቡ ከጊዮርጊስ ጋር በሚኖረዉ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተሰልፎ እንደሚጫወትም ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።
ከዚህ በፊት ሁለቱ ተጫዋቸኦች ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የአራት ወር የጨዋታ እዕዳ እና የ200ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ጥሎባቸዉ እንደነበር አይዘነጋም።
አስተያየት ይስጡ