ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለት ተጫዋች ውል ሲያራዝም አዲስ ተጫዋችም አስፈረመ።

በአሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ የሚመሩት እና በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ከዘንድሮ በተሻለ በቀጣይ ለማጠናቀቅ ይረዳቸው ዘንድ በርካታ ዝውውሮችን እየፈፀሙ የሚገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች የ2018 የውድድር ዘመን የአመቱ ኮከብ ጎል አግቢ ሆና የጨረሰችውን አጥቂዋ ዳግማዊት ሠለሞን እና የተከላካይ አማካዩዋን ሀና ሲሳይን ውል ለተጨማሪ አመት ሲያራዝም የቀድሞው የሀዋሳ ፣ ንግድ ባንክ እና በመቻል ያለፉትን አመታት ቆይታ የነበራትን የአማካይ ተከላካይ እና ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነችውን ብርቄ አማረን በይፋ አስፈርሟል።
አስተያየት ይስጡ