በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የወረደው ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውጭ ሆኗል።

በፋይናንስ እና በተለያዩ ምክንያቶች ካለፈው አመት ጀምሮ ችግር ውስጥ የነበረው ምድረ ገነት ሽረ ዘንድሮ አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃን በመቅጠር ለጥቂት ቀናት ብቻ ልምምድ ከሰራ በኋላ ወደ ውድድር ለመግባት እሳቤ ቢሆንም የክለቡ ተደራራቢ ችግሮች ከውድድሩ ውጪ እንዲሆን አድርጎታል። ስለሆነም ከአሁን በኋላ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በ19 ክለቦች ብቻ የሚቀጥል ይሆናል ።
አስተያየት ይስጡ