መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ ላይቤሪያዊያን ዳኞች የሱዳን እና ኢትዮጵያን ጨዋታ ይመራሉ
ዋልያዎቹዜናዎች

ላይቤሪያዊያን ዳኞች የሱዳን እና ኢትዮጵያን ጨዋታ ይመራሉ

አጋራ
አጋራ

ኢትዮጵያ ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከሱዳን ጋር ስታደርግ የፊታችን ዓርብ መስከረም 15 ማታ 1 ሰዓት ላይስታከናውን አራቱም ዳኞች ከላይቤሪያ መሆናቸው ታውቋል።

በዋና ዳኝነት ዋሸንግተን ዶሎ ፣ በረዳት ዳኝነት ደግሞ ጆኤል ዶ እና ቶማስ ኤን ኮነህ ሲመደቡ ሞሰስ ቢ ጆንሰን በአራተኛ ዳኝነት ተመድቧል። በምድብ 10 ከሱዳን ፣ ሴኔጋል እና ሞዛምቢክ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ የምድቡን 2ኛ ጨዋታ ደግሞ በዕለተ ማክሰኞ በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ከሴኔጋል ጋር የምታደርግ ይሆናል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከ14 አመት በፊት በማከናወን ካርቱም ላይ ሱዳን 5 ለ3 ስታሸንፍ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው ደግሞ ኢትዮጵያ 2 ለ 0 አሸንፋ ከ31 አመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫውን መቀላቀሏ ይታወሳል። ከ14 አመታት በኋላ ምን ተአምር ይፈጠር ይሆን ?

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...