ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋችን ውል ደግሞ አራዝሟል።
በካፍ የሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያን የሚወክለው የዘጠኝ ጊዜ አሸናፊው እና የምድብ ድልድሉን ያወቀው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ከተማ ለውድድሩ ሲያደርግ የነበረውን ልምምድ አጠናቆ የፊታችን ነሀሴ 13/2018 ውድድሩ ስፍራ የሚያመራ ሲሆን ቡድኑን ማጠናከሩንም ቀጥሎ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋችን ውል ደግሞ አራዝሟል።

በአጥቂ ሰፍራ ላይ ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከተገኘ በኋላ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ስትጫወት የምናውቃት አጥቂዋ ማህሌት ምትኩ በአዳማ ሀዋሳ እና የተጠናቀቀውን አመት በኤሌክትሪክ የተጫወተችው የመስመር ተከላካዩዋ በሻዱ ረጋሳ እና ወደ ቀድሞው ክለቧ ከአመታት በኋላ ከአዲስ አበባ ከተማ የተቀላቀለችው የመስመር ተከላካዩዋ አለምነሽ ገረመው ክለቡን በይፋ በሁለት አመት ውል መቀላቀል ችለዋል።
ክለቡ ከሦስቱ አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የግብ ጠባቂዋን አበባ አጄቦን ውልም አራዝሟል። ንግድ ባንክ እስከ አሁን ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል።
አስተያየት ይስጡ