የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሊጉን ከመሠረቱ ክለቦች መካከል አንዱ የነበረው ሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድን የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ ለሁለት አመታት ቀጥሯል።

ሊጀመር አስራ ሦስት ቀናት በቀሩት የ2019 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሊጉን ከመሠረቱ ክለቦች መካከል አንዱ የነበረው ሀዋሳ ከተማ ገና አዲስ አሰልጣኝ በዛሬው ዕለት ቀጥሯል።
ከ2004 እስከ 2011 ድረስ ለስምንት ተከታታይ አመታት ሀዋሳ ከተማን የመራው እና በመቀጠል በአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ጭምር ያገለገለውን አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድን ከሰባት አመታት በኋላ ቆይታ ባደረገው መልካሙ ታፈረ ምትክ ዳግም የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ ለሁለት አመታት ቀጥሯል።
አስተያየት ይስጡ