መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲያደርግ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቻል ነጥብ ተጋርተዋል።
ሀዲያ ሆሳዕናመቻልቅዱስ ጊዮርጊስወልዋሎየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲያደርግ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቻል ነጥብ ተጋርተዋል።

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሉን ሲያስቀጥል፣ መቻል የመሪነት እድሉን አምክኗል!

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-0 ሀድያ ሆሳዕና

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን 2-0 በመርታት የድል ጉዞውን ማስቀጠል ችሏል።በጨዋታው የበላይነቱን በመያዝ የጀመረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ9ኛው ደቂቃ ተመስገን ብርሃኑ ወደ ጎል ያሻማትን ኳስ የሀድያ ሆሳዕናው ተጫዋች ዳግም ወንድሙ በራሱ ጎል ላይ በማስቆጠሩ መሪነቱን ወስዷል።ፈረሰኞቹ ጫናቸውን በመቀጠል የተከላካዮቹ ስተት በመጠቀም በ44ኛው ደቂቃ ቢላል ገመዳ በጥሩ ሁኔታ ያመቻቸውን ኳስ አማኑኤል ኤርቦ ወደ ጎልነት በመቀየር የቡድኑን መሪነት ወደ 2-0 አሳድገዋል።ሀድያ ሆሳዕና በመጀመሪያው አጋማሽ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ሳይችል ወደ ዕረፍት አምርቷል።ከዕረፍት መልስ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ቢያሳይም ጎል ማስቆጠር አልቻለም። ሀድያ ሆሳዕና በዙም ሙከራ ሳያደርግ በመጨረሻም ጨዋታው በፈረሰኞቹ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 0-0 መቻል

በዚህም መቻል የሊጉን መሪነት ለመያዝ የነበረውን ዕድል መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።
በመጀመሪያው አጋማሽ መቻል ከኋላ ኳስ መስርቶ ለመጫወት ሲቸገር ታይቷል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአብዛኛው ትኩረቱን በመከላከል ላይ በማድረግ አጋማሹ ያለ ጎል እንዲጠናቀቅ አድርጓል።ከዕረፍት መልስ መቻል የማጥቃት እንቅስቃሴውን ማሻሻል ቢችልም በ62ኛው ደቂቃ በረከት ካሌብ በስምዖን ማሩ ላይ በሰራው ጥፋት ሁለተኛ ቢጫ ካርድ ተመልክቶ ከሜዳ ተሰናብቷል።በዚህም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የቁጥር ብልጫ ቢያገኝም ወደ ጎልነት መቀየር አልቻለም። መቻልም በተጫዋች ብልጫ ስር ቢገባም ውጤቱን መቀየር ሳይችል ጨዋታው 0-0 ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...