መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እና ያሬድ ባየህ ከነገው ጨዋታ በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ዋልያዎቹዜናዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እና ያሬድ ባየህ ከነገው ጨዋታ በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አጋራ
አጋራ

“አጋጣሚዎችን ያለመጠቀም ችግር የሚቀረፈው ትኩረት በማድረግ ነውና በዚያ ጉዳይ ላይ ተወያይተናል”  አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

“በደጋፊዎቻችን ፊት መጫወት እጅጉን ይጠቅመናል ያለው” አምበሉ ያሬድ ባዬ

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ “በሱዳኑ ጨዋታ የነበረብን አጋጣሚዎችን ያለመጠቀም ችግር የሚቀረፈው ትኩረት በማድረግ ነውና በዚያ ጉዳይ ላይ ተወያይተናል” ሲሉ ተናግረዋል።
ግብ የማስቆጠር ችግራችን የሚቀረፈው ተጫዋቾች በሚያድርባቸው የራስ መተማመን መሆኑንም ነው የገለፁት። “የእኛ ስራ ኳሱ ሳጥን ውስጥ እንዲደርስ እና አጋጣሚዎች እንዲፈጠሩ ማድረግ ነው” ሲሉም አክለዋል።
ለተጫዋቾችም ውሳኔ በመወሰን በኩል ነፃነት እንደተሰጣቸውም ተናግረዋል። “ሴኔጋል ትልቅ ቡድን ቢሆንም በህዝባችን ፊትና በሜዳችን ስለምንጫወት ባለ ድል ለመሆን ወደ ሜዳ እንገባለን። አሸናፊውን የ90 ደቂቃው ፍልሚያ ይወስነዋል” ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
“በደጋፊዎቻችን ፊት መጫወት እጅጉን ይጠቅመናል ያለው” አምበሉ ያሬድ ባዬ በበኩሉ ሴኔጋልን ለማሸነፍ መዘጋጀታቸውን ገልጿል።
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መስፍን ታፈሰ እና በረከት ወልዴ ከነገው ጨዋታ ውጭ መሆናቸውን ተናግረዋል። መስፍን በቢጫ እንዲሁም በረከት በጉዳት ምክንያት ነው የማይሰለፉት።

በተያያዘ ዜና ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ዋልያዎቹ ጨዋታውን ካሸነፉ ለእያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ሽልማት ሽልማት ይበረክትላቸዋል ብለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...