በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውሳኔ በረከት ደስታ መቻልን ለቆ ሀዋሳን ተቀላቀለ

እግር ኳስን ከአዳማ ከተማ ከጀመረ በኋላ በፋሲል ከነማ እና እንዲሁም ደግሞ ያለፉትን ሁለት አመታት በመቻል ቆይታን ማድረግ የቻለው የመስመር አጥቂው በረከት ደስታ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት በመቻል ውሉን አራዝሞ የነበረ ቢሆንም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ወደ ክለቡ ካምፕ ተጫዋቾች በተባለው ቀን እንዲገቡ ጥሪ አድርገው ዘግይቶ መድረሱን ተከትሎ ከአሰልጣኙ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት መቻልን በመልቀቅ ለአሰልጣኝ ተመስገን ዳናው ሀዋሳ ከተማ ፊርማውን አኑሯል።
አስተያየት ይስጡ