ሀድያ ሆሳዕና ተጨማሪ ተጫዋች የግሉ አደረገ።
በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ በቀጣዩ የውድድር ዘመን እንደሚመራ የሚጠበቀው ሀድያ ሆሳዕና ከአጥቂው ቢያንም ጌታቸው ቀጥሎ ሁለተኛው ፈራሚ የመስመር አጥቂው እዮብ ገብረማርያም ሆኗል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን እና ሻሸመኔ ከተማ ተጫዋች ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለት አመት ቆይታ በኋላ ቀጣዩ ክለቡ በሁለት አመት ውል ሀድያ ሆሳዕና መሆኑን ክለቡ በይፋ ያደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ