መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ የጨዋታ ዘገባ | የመናፍ ዐወል ብቸኛ ግብ ባህርዳር ከተማን አሸናፊ አድርጓል
ባህርዳር ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | የመናፍ ዐወል ብቸኛ ግብ ባህርዳር ከተማን አሸናፊ አድርጓል

አጋራ
አጋራ

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ባህርዳር ከተማን ከድሬዳዋ ከተማ አገናኝቶ መናፍ ዐወል ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ የጣና ሞገዶቹ ማሸነፍ ችለዋል ።

ባህርዳር ከተማዎች በ27ኛው ሳምንት በሀዋሳ ከተማ በተረቱበት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶስት ለውጦችን በማድረግ አቡበከር ኑሪ ፤ ሰለሞን ወዴሳ ፤ ሳለአምላክ ተገኝ ፤ አደም አባስን እና ፋአድ ፈረጃን በፋሲል ገብረሚካኤል ፤ ፈቱዲን ጀማል ፤ ግርማ ዲሳሳ ፤ አለልኝ አዘነ እና ተመስገን ደረሰ ምትክ ሲያሰልፉ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ደግሞ በሳምንቱ በአርባምንጭ ከተማ በተሸነፉበት ጨዋታ ከነበረው ምርጥ 11 ሁለት ለውጦችን በማድረግ እንየው ካሳሁን እና ዳንኤል ደምሴን በማሳረፍ ያሲን ጀማል እና አቤል አሰበን በቋሚ አሰላለፍ አካተው ጨዋታውን መጀመር ችለዋል ።

የሳምንቱ ቀዳሚ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ካለባቸው የመውረድ ስጋት አንፃር ተጠባቂ እና ለባህርዳር ከተማም ሆነ ለድሬዳዋ ከተማ ወሳኝ ነበር ። ይህም በጨዋታው የሜዳ እንቅስቃሴ ላይ በግልፅ የታየ ነበር ። ባህርዳር ከተማ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመድረስ አንፃራዊ የበላይነት ነበራቸው ።

በድሬዳዋ ከተማ በኩል የባህርዳር ከተማ የፊት መስመር ተጫዋቾች ክፍተቶችን እንዳያገኙ በማድረግ ረገድ የተሳካ ጊዜን ሲያሳልፉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በፈጣን እንቅስቃሴዎች ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረቶችን አድርገው ነበር ።

የግብ ሙከራዎችን እምብዛም ሳያስመለክተን የቆየው ጨዋታ 32ኛው ደቂቃ ላይ ቀዳማዊ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ አስተናግዷል ። የድሬዳዋ ከተማው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤ ከሳጥን ውጪ ያደረገው የግብ ሙከራ በአቡበከር ኑሪ ተይዟል ።

ከመጀመሪያው ሙከራ ስምንት ደቂቃዎች በኋላ የመጀመሪያ ግብ ከመረብ አርፏል ። ባህርዳር ከተማዎች ያገኙተን የቅጣት ምት ወደ ግብ ሞክሮ አደም አባስ ያገኘው ኳስ በአህመድ ረሺድ በኩል አልፎ የመሀል ተከላካዩ መናፍ ዐወል ኳስ እና መረብን አገናኝቷል ።

 

የመጀመሪያው አጋማሽም በጣና ሞገዶቹ 1 – 0 መሪነት ተጠናቋል ።

የሁለተኛው አጋማሽም በባህርዳር ከተማ አንፃራዊ የበላይነት የተጀመረ ሲሆን ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ የግብ ዕድሎችንም መፍጠር የቻሉበት ነበር ። በአጋማሹ ቀዳሚ ሙከራ ኤርትራዊው አሊ ሱሌማን የድሬዳዋ ከተማ ተከላካዮች በተዘናጉበት ወቅት ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ መሞከር ቢችልም ፍሬው ጌታሁን አድኖበታል ።

በ57ኛው ደቂቃ ላይም አሊ ሱሌማን ሌላ ዕድል አግኝቶ ሳይጠቀምበት ሲቀር ከአንድ ደቂቃ በኋላ ደግሞ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ከማዕዘን ምት የተሻገረን ኳስ ማማዱ ሲዲቤ ገጭቶ አህመድ ረሺድ ግብ ከመሆን ለጥቂት አድኖታል ።

ብርቱካናማዎቹ ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ ቀድሞ ከነበራቸው የማጥቃት እንቅስቃሴ በተሻለ ወደ ባህርዳር ከተማ የግብ ክልል ለመድረስ አና የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ሲታትሩ ቆይተዋል ። ነገር ግን እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስም ይህ ነው ሊባል የሚችል አቡበከር ኑሪን የፈተነ የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም ነበር ።

መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተጨመሩ አራት ደቂቃዎች ላይ ከማዕዘን የተነሳ ኳስን ማማዱ ሲዲቤ ሲገጨው ሱራፌል ጌታቸው አግኝቶ ከመረብ ማሳረፍ ቢችልም የዕለቱ የመሀል ዳኛ ተፈሪ አለባቸው ግቡን ሰያፀድቁት ቀርተዋል ። በመጨረሻም ባህርዳር ከተማ ከጨዋታው ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል ።

ውጤቱን ተከትሎ ባህርዳር ከተማ ነጥቡን 33 በማድረስ ወደ 9ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ በነበረበት 29 ነጥብ እና 14ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።

በ29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ሰኔ 19 ( ዕሁድ ) ከቀኑ 10:00 ላይ ባህርዳር ከተማ ከሰበታ ከተማ ሲጫውት ከሁለት ቀናት በኋላ ሰኔ 21 ( ማክሰኞ ) በተመሳሳይ 10:00 ድሬዳዋ ከተማ አዳማ ከተማን የሚገጥም ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...