ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ27ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማከሰኞ ሰኔ 14 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በተጫዋቾች መኳንንት ካሳ(ሲዳማ ቡና) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያሰጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ እንዲሁም ያሬድ ባየህ(ፋሲል ከነማ) በ5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከተ ተመሳሳይ 1 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
በክለቦች ሲዳማ ቡና የክለቡ አምስት ተጫዋች በሳምንቱ ጨዋታ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሰበታ ከተማ በ27 ኛ ሳምንት ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ የክለቡ ቡድን መሪ ባለመገኘቱ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ክለቡ ብር 5000/አምስት ሺህ/ እንዲቀጣ ተወስኗል።
ዋና ዳኞች ቢኒያም ወርቅአገኘው ፣ ተካልኝ ለማ እና ዳንኤል ግርማይ ሰኔ 7 2014 ዓ.ም በተደረገው የ26ኛ ሳምንት ቅድመ ጨዋታ ስብሰባ ላይ ስላለመገኘታቸው ሪፖርት የቀረበባቸው በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት እያንዳንዳቸው ብር 1000/አንድ ሺህ/ እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፏል።
አስተያየት ይስጡ