ሶሰቱን የትግራይ ክለቦች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንዲመለሱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሰጠው ትእዛዝን የተመለከተው የፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ቦርድ በጉዳዩ ላይ ሙሉ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ መራው።
በመንግስት በኩል ያለውን ሃሳብ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለፌዴሬሽኑ አቅርቦ ፌዴሬሽኑ ሶስቱ ክለቦች መቀለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራትና ስሁል ሽረ ያለምንም መመዘኛ በ2017 ወደ ሊጉ እንዲመለሱና የ2017 የሊጉ ክለቦች ቁጥር 19 እንዲሆኑ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።
ከፌዴሬሽኑ የደረሰውን ደብዳቤ ዛሬ የተመለከቱት የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አባላት በውሳኔው ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ የማህበሩ አባላት የሆኑ 16 ክለቦች የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጡበት ለጠቅላላ ጉባኤው መርቶታል።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አክሲዮን ማህበሩ ባደረገው ስብሰባ በቅርቡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት መንግስት በጠየቀውና ፌዴሬሽኑ አቅጣጫ ባስቀመጠበት ውሰኔ ዙሪያ ምላሽ ለመስጠት መስማማቱ ታውቋል።