የአዳማ ከተማው ውጤታማ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ።
በአዳማ ከተማ ያልጨረሰው የቤት ስራ ቢኖርም የክለቡ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አንበሴ እንፈልገዋለን ቢሉም ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ባለመቻላቸው ድሬዳዋ ከተማዎች ረዘም ካለ ኮንትራትና የተሻለ ከሚባል ደመወዝ ጋር የመልበሻ ቤት አለቃቸው እንዲሆን በመወሰን ነገ ጠዋት በሸራተን አዲስ ስምምነታቸውን በፊርማቸው ለማረጋገጥ ቀጠሮ ይዘዋል።
ደመወዝ ያልተከፈላቸውና የመጫወት ሞራላቸው የተነኩትን ተጨዋቾች እያባባለና እያግባባ ቡድኑን የተሻለ ደረጃ ላይ ያደረሰው አሰልጣኙ የደመወዝ ያለመክፈል ጥያቄ የማይነሳበትን ድሬዳዋ ከተማን ለማሰልጠን መስማማቱ የተሻለ የስራ ነጻነት የሚፈጥርለት ይሆናል ተብሏል።
በወጣቶች ላይ ባለው እምነት የሚታወቀው አሰልጣኝ ይታገሱ የአዲሱ ክለቡ አመራሮች የድሬዳዋ እግርኳስ አፍቃሪያን የሚደመሙባቸውን ወጣቶች የማፍራት ስራውን በነጻነት እንዲሰራ ይፈቅዱለታል ተብሎ ይጠበቃል።