በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለ15 ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ገናና የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ደከም ብሎ ታይቷል።
ቡድኑ በ23ኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታም በትናንትናው ዕለት ሀዋሳ ከተማን ገጥሞ 2 – 1 በመሸነፍ የውድድር አመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
የክለቡ ቦርድ አመራር በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባም ዋና አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታን እና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙን ውብሸት ደሳለኝን በጊዜያዊነት ከስራቸው ማገዱን ይፋ አድርጓል።
በዚህም ምክትል አሰልጣኙ ደረጄ ተስፋዬ በጊዜያዊነት ቡድኑን እንዲመሩ የተሾሙ ሲሆን የወጣት ቡድኑ አሰልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ በምክትል አሰልጣኝነት ተሹመዋል።
- ማሰታውቂያ -
ቅዱስ ጊዮርጊስ በ24ኛው ሳምንት መርሐግብር በመጪው አርብ ከኢትዮጵያ መድኅን ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።
በ23 ጨዋታዎች 39 ነጥቦችን የሰበሰበው ቡድኑ በደረጃ ሰንጠረዡ 4ኛ ላይ ተቀምጧል።