By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: መቻል በምንይሉ ወንድሙ ሀትሪክ ታግዞ ወልቂጤ ከተማን ሲረታ ፤ ሀዋሳ ከተማም ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሸነፍ ችሏል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስሀዋሳ ከተማወልቂጤ ከተማየጨዋታ ዘገባመቻል

መቻል በምንይሉ ወንድሙ ሀትሪክ ታግዞ ወልቂጤ ከተማን ሲረታ ፤ ሀዋሳ ከተማም ቅዱስ ጊዮርጊስን ማሸነፍ ችሏል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ23ተኛ ሳምንት መርሐግብር መቻል በምንይሉ ወንድሙ ሀትሪክ ወልቂጤ ከተማን ሶስት ለአንድ አሸንፏል ።

ቀን ዘጠኝ ሰዓት ሲል በጀመረዉ የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች በተመጣጠነ የጨዋታ እንቅስቃሴያቸዉን ከጀመሩ በኋላ በመጀመሪያዉ ተጠቃሽ ሙከራ መቻሎች በ13ተኛዉ ደቂቃ ላይ መሪ መሆን ችለዋል ። በዚህም በዚሁ ደቂቃ ላይ በመልሶ ማጥቃት የተገኘዉን ኳስ ከንዓን ማርክነህ በፍጥነት ለምንይሉ ወንድሙ አቀብሎት ተጫዋቹ ደግሞ በቀጥታ ወደ ግብነት በመቀየር መቻልን መሪ ማድረግ ችሏል።

እንደከዚህ ከደቀሙ የማጥቃት እንቅስቃሴያቸዉ እየተዳከመ የቀጠሉት ወልቂጤ ከተማዎች ይባስኑ በ24ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ አስተናግዷል ። በዚህም ከግራ መስመር በኩል ዳዊት ማሞ ያቀበለዉን ኳስ አምበሉ ምንይሉ ወንድሙ በድጋሚ ወደ ግብነት በመቀየር የክለቡን መሪነት ወደ ሁለት ለዜሮ ከፍ ማድረግ ችሏል።

- ማሰታውቂያ -

ገና በጊዜ ሁለት ግብ የተቆጠረባቸዉ ወሎቂጤዎች በ33ተኛዉ ደቂቃ ላይ ወደ ጨዋታዉ የሚመልሳቸዉን ለማግኘት ተቃርበዉ ነበር ፤ በዚህም ተመስገን በጅሮንድ ኳስ በዕጅ መነካቱን ተከትሎ የተገኘዉን የቅጣት ምት ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ግን ለጥቂት ወጥታለች። በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ ላይም በ43ተኛዉ ደቂቃ ምንይሉ ወንድሙ ሶስተኛ ግብ ለራሱ እና ለክለቡ አስቆጥሮ አጋማሹ በመቻል ሶስት ለዜሮ መሪነት ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ መንቀሳቀስ የጀመሩት ወልቂጤዎች ምንም እንኳን በአንድ ሁለት አጋጣሚ ወደ ሶስተኛዉ የሚዳ ክፍል ቢገቡም ነገር ግን ዕድሎችን ከመጠቀም እንፃር ደካማ ሆነዉ ተስተዉሏል። በ68ተኛዉ ደቂቃ ላይም መድን ተክሉ በክትፎዎቹ በኩል ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ ኳሷን አዉጥቷት በ76ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግን ጋዲሳ መብራቴ ከቅጣት ምት ድንቅ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው ሶስት ለአንድ በሆነ ዉጤት በመቻል አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሀዋሳ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ለአንድ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል ።

በፈረሰኞቹ የተሻለ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ አመሻሽ 12:00 ሰዓት ሲል በጀመረዉ ጨዋታ በ10ኛዉ ደቂቃ ላይ አጥቂዉ አማኑኤል ኤረቦ ወደ ግራ ካደላ ቦታ ከሳጥን ዉጭ ድንቅ ሙከራ ማድረግ ቢችልም ግብ ጠባቂዉ ቻርልስ ግን በደረቱ መልሶበታል። በዚህ ሂደት በጀመረዉ ጨዋታም በ14ተኛዉ ደቂቃ ላይ ፈረሰኞቹ ግብ አግኝተዋል ከኋላ መስመር ዳዊት ተፈራ የሰነጠቀለትን ኳስ አማኑኤል አረቦ በፍጥነት ተቆጣጥሮ ቺፕ አድርጎ በማስቆጠር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

ከግቧ መቆጠር ከአምስት ያህል ደቂቃዎች በኋላ ሀዋሳ ከተማ ድንቅ ሙከራ አድርገዋል ፤ በዚህም እንየዉ ካሳሁን ከቅጣት ምት ያሻማዉን ኳስ በረከት በግንባሩ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ግብ ጠባቂዉ ባህሩ ነጋሽ ኳሷን ተቆጣጥሯል። በ33ተኛዉ ደቂቃ ላይም አሊ ሱለይማን ከሳጥን ዉጭ ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችሎ ነበር። በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ በ43ተኛዉ ደቂቃ ላይ አማኑኤል አረቦ አስቆጪ ሙከራ አድርጎ ግብ ጠባቂዉ ቻርልስ እንደምንም አዉጥቶበት ለዕረፍት ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

በሁለተኛዉ አጋማሽ ተጋግለዉ የተመለሱት ሀይቆቹ በአጥቂዎቹ አሊ ሱለይማን እና እስራኤል እሸቱ አማካኝነት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ካደረጉ በኋላ በ68ተኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ማስቆጠር ችለዋል ። በዚህም ከተከላካይ ክፍል የተሻገረለትን ኳስ አሊ ሱለይማን በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን አቻ አድርጓል። ከመጀመሪያዉ አጋማሽ በተቃራኒዉ ተቀዛቅዘዉ የተመለሱት ፈረሰኞቹ በ84ተኛዉ ደቂቃ ላይ ተጨማሪ ግብ አስተናግደዋል። በዚህም ሄኖክ አዱኛ በመከላከል እንቅስቃሴ ለመመለስ የገጨዉን ኳስ አጠገቡ የነበረዉ አማኑኤል ጎበና አግኝቶት ወደ ግብነት በመየቀር ክለቡን ከመመራት ወደ መሪነት አሸጋግሮ ፤ ጨዋታዉም በሀዋሳ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን ሲያሸንፍ ፤ ፋሲል ከነማም ከተከታታይ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል ተመልሷል !!
Next Article ቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኙ እና የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙን ከኃላፊነታቸው አገደ

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎች

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ቀጣይነት ?

kidus Yoftahe By kidus Yoftahe 6 years ago
የሀድያ ሆሳዕና ክለብ ከተጫዋቾች ክፍያ ጋር በተያያዘ በድጋሚ ችግር ውስጥ ገብቷል
ጋቶች ፓኖም የኢራቁን ክለብ በአንድ ዓመት ውል ተቀላቀለ
ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና አሁንም ማሸነፍ ተስኖታል።
ሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ ወደ ሀዋሳ እንዲመለስ አዘዘ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?