የቅዱስ ጊዪርጊሱ ምክትል አሰልጣኝ ሆኖ ያገለገለው አዲስ ወርቁ ለሱዳኑ ትልቅ ክለብ አልሂላል ለቀጣዮቹ ሁለት አመት ለመስራት ፊርማውን አኑሯል።
በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ለሱዳኑ አልሂላል ም/ል አሰልጣኝና የፐርፎርማንስ አናሊስት ሆኖ የሚሰራ ሲሆን በቀናት ውስጥ ወደ ሱዳን ያቀናል ተብሎ ይጠበቃል። ”
” በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በነበረኝ ሚና ደስተኛ ነኝ ኩራት ይሰማኛል የፈረሰኞቹ የቡድን አባላት አመራሮች ደጋፊዎች ስራውን በነጻነት እንድሰራ ስራዬን እንድወድ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ” ብሏል።
ፈረሰኞቹ ኢትዮዽያ እግርኳስ ላይ ያላቸው የበላይነት አልሂላልም በሱዳን ያለው በመሆኑ ይህን ዝውውር ከትልቅ ክለብ ወደ ትልቅ ክለብ የተደረገ ዝውውር ተብሎ ተወስዷል።