መነሻ ገጽ ቡርኪናፋሶ “ጨዋታው ለኛ የሞት ሽረት ፍልሚያ እንደሆነ እንረዳለን፤ ማለፍና መውደቃችን የሚወሰነው በዛሬው ጨዋታ ነው፡፡”/ካሙ ማሎ የቡርኪናፋሶ ዋና አሰልጣኝ/
ቡርኪናፋሶአፍሪካአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹዜናዎች

“ጨዋታው ለኛ የሞት ሽረት ፍልሚያ እንደሆነ እንረዳለን፤ ማለፍና መውደቃችን የሚወሰነው በዛሬው ጨዋታ ነው፡፡”/ካሙ ማሎ የቡርኪናፋሶ ዋና አሰልጣኝ/

አጋራ
አጋራ

“ጨዋታው ለኛ የሞት ሽረት ፍልሚያ እንደሆነ እንረዳለን፤ ማለፍና መውደቃችን የሚወሰነው በዛሬው ጨዋታ ነው፡፡”

“ጨዋታው መረጋጋትን እንዲሁም ታጋይነትን ይጠይቃል። ይህን ሁሉ ለማድረግ አምነን ነው ዛሬ ወደሜዳ የምንገባው።”ካሙ ማሎ /የቡርኪናፋሶ ዋና አሰልጣኝ/

ይህን ያሉት የዛሬ ተጋጣሚያችን የቡርኪናፋሶ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ካሙ ማሎ ናቸው፡፡በኮቪድ 19 የተነሳ እስካሁን ድረስ ሙሉ ተጫዋቾቻቸውን ማግኘት ያልቻሉት ካሙ ዛሬም የክለቡን ዋና ግብ ጠባቂ ሄርቬ ኩዋኩ ኮፊን አገልግሎት ማግኘት አይችሉም፤ እርሳቸውም ቢሆኑ ቡድናቸው የመጀመሪያውን ጨዋታ ከካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ጋር ሲያደርግ ካሙ በኮቪድ ምክንያት ራሳቸውን አግልለው ከሆቴላቸው በቴሌቪዥን ነው ጨዋታውን የተመለከቱት፡፡

« የዛሬው መልካም ዜና አምበላችን በርትሮ ትራኦሬ ከቫይረሱ ነጻ መባሉ ነው፡፡ ዛሬ መሰለፍ ይችላል፤ በተጨማሪም ሁለቱንም ጨዋታዎች ማቆያ ውስጥ የነበሩት ዳንጎ ዋታራ፣ ሱማይላ ዋታራ እና ሳይዱ ሰምፖሬ ከቫይረሱ ነጻ ተብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ግብ ጠባቂያችን ሄርቬ ኩዋኩ ኮፊ ዛሬ ግልጋሎት ሊሰጠን አይችልም፡፡» ካሙ ጨምረው እንደገለጹት እንዳለመታደል ሆኖ የሄርቬን አገልግሎት ዛር ልናገኝ አንችልም ብለዋል፡፡

ተጋጣሚያቸውን በሚመለከት አስተያየት የሰጡት ካሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደካሜሮን የመጣው ለቱሪዝም እንዳልሆነ እናውቃለን ብለዋል፡፡ በወረቀት ላይ ትላልቅ ቡድኖች ብለህ የምታስቀምጣቸው ሃገራት በዚህ የአፍሪካ ዋንጫ በደረጃ በብዙ የሚቀድሟቸው ቡድኖች ማሸነፍ ሲቸገሩ አይተናል፡፡ ሁሉንም ብሄራዊ ቡድን ማክበር ያስፈልጋል፡፡ ጨዋታው ቀላል እንደማይሆን እገምታለው ለኛ ግን ማሸነፍ ግዴታችን ነው፡፡

የሁለቱ ሃገራት ጨዋታ ዛሬ ምሽት አንድ ሰዓት በባፉሳም ከተማ ኩኮንግ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ሁለቱ ሃገራት ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ጨዋታ እንደነበር ይታወሳል፤ ድል ለዋልያዎቹ !

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...