መነሻ ገጽ ቡርኪናፋሶ ከምሽቱ የቡርኪናፋሶ እና የዋልያዎቹ ጨዋታ አስቀድሞ ቁጥራዊ መረጃዎች !!
ቡርኪናፋሶአፍሪካአፍሪካ ዋንጫዋልያዎቹዜናዎች

ከምሽቱ የቡርኪናፋሶ እና የዋልያዎቹ ጨዋታ አስቀድሞ ቁጥራዊ መረጃዎች !!

አጋራ
አጋራ

በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ የሚካሄዱ ሲሆን በምድብ አንድ የምትገኘዉ ኢትዮጵያም ከቡርኪናፋሶ አቻዋ ጋር በባፉሳ ከተማ በሚገኘዉ ኩኮንግ ስታዲየም ከምሽቱ 1:00 ላይ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ሞሪሽየሳዊዩ አህመድ ራሂላል በሚመሩት ጨዋታም ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድልን ይዘዉ ይጫወታሉ። በዋልያዎቹ በኩል ወደ ቀጣዩ ዙር ለመሻገር ጨዋታውን አሸንፈዉ በተቃራኒው የካሜሩንን እና የኬፕ ቨርዴ የጨዋታ ዉጤት እንዲሁም የግብ መጠን የሚጠብቁ ሲሆን ፤ በተጋጣሚያቸው ቡርኪናፋሶዎች በኩል ደግሞ ጨዋታዉን ማሸነፍ በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፋቸው ሲሆን ፤ አቻ መዉጣት ደግሞ በተመሳሳይ የካሜሩንን እና ኬፕ ቨርዴን የጨዋታ ዉጤት እንዲጠብቁ ያስገድዳቸዋል።

ከምሽቱ ተጠባባቂ ጨዋታ አስቀድሞም ቁጥሮች ስለ ሁለቱ ሀገራት ምን ይላሉ:-

ቡርኪናፋሶ እና ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2013ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ የተገናኙ ሲሆን ጨዋታዉንም ቡርኪናፋሶን 4-0 አሸንፋለች። ይሄ ዉጤትም ለቡርኪናፋሶዎች በመድረኩ ላይ እስከ ዛሬ ያስመዘገቡት ትልቁ ድል ነው።

ቡርኪናፋሶ በአፍሪካ ዋንጫ በምድብ ድልድል ካደረጋቻቸው 5 ጨዋታዎች አንዱን ብቻ የተሸነፈች ሲሆን ብቸኛዉ ሽንፈታቸዉ ደግሞ በአፍሪካ ዋንጫዉ መክፈቻ ዕለት በካሜሩን 2ለ1 የተሸነፉበት ነበር።

ቡርኪናፋሶዎች ዛሬ የሚያሸንፉ ከሆነም ከየካቲት 1998 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድር መድረኩ ላይ ተከታታይ የምድብ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይችላሉ።

በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ለቡርኪናፋሶ ከጉስታቮ ሳንጋሬ በላይ የግብ እድሎችን የፈጠረ ተጫዋች የለም። በዚህም እስካሁን ከቡድን አጋሮቹ በበለጠ በ10 የግብ ዕድሎችን መፍጠር ችሏል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫዉ ባደረገቻቸው ያለፉት 10 ጨዋታዎች ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለችም (3 አቻ 7 ተሸንፋለች ) በተጨማሪም ያለፉትን 4 ጨዋታዎችን በተከታታይ ሽንፈት አስተናግዳለች።

በዚህም ኢትዮጵያ በታሪኳ ረጅም የሽንፈት ጉዞዋ ከነበረዉ እና (በ1968 እና 1970 ) መካከል በተደረጉት ጨዋታዎች ያጋጠማት የአምስት ጨዋታዎች ሽንፈት ሲሆን ዛሬ ምሽት ከተሸነፈችም ከዚያ ጊዜ ጋር እኩል ይሆናል።

በአፍሪካ ዋንጫዉ ላይ ከኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች መካከል ብዙ ንክኪዎችን (128)፣ 110 ቅብብሎች እንዲሁም 9 ኳሶችን በማፅዳት ተከላካዩ ምኞት ደበበ ቀዳሚው ነዉ።

🇪🇹መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን 🇪🇹

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...