መነሻ ገጽ ሪፖርት የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማና ወልቂጤ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል
ሪፖርትቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማወልቂጤ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማና ወልቂጤ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

አጋራ
አጋራ

በሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ሶስተኛ ጨዋታ የተገናኙት አዳማ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ በአንድ አቻ ውጤት ተለያይተዋል ።

በዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ 9 ሰዓት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቀዝቀዝ ያለ እንቅስቃሴ ያስመለከት ነበር ። 10ኛ ደቂቃ ላይ አዳማ ከተማ ያገኘውን የማዕዘን ምት በሚመታበት ሰዓት በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ እስራኤል እሸቱ በሚሊዮን ሰለሞን ላይ በሰራው ጥፋት ምክንያት አዳማ ከተማዎች የፍፁም ቅጣት ምት ቢያገኙም አምበሉ ዳዋ ሆቴሳ ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።

በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ጊዜ ወልቂጤ ከተማዎች ከአዳማ ከተማ ተጫዋቾች በተሻለ መልኩ ኳሱን በመቆጣጠር ወደ ጎል ለመድረስ ሞክረዋል ። በአዳማ ከተማ በኩልም ወደ ግብ ለመድረስ ያደረጓቸው ሙከራዎች በወልቂጤ ከተማ የተከላካይ መስመር እና ከጨዋታ ውጪ በመሆን ይበላሹባቸው ነበር ። 30ኛ ደቂቃ ላይ በወልቂጤ ከተማ በኩል የተገኘው የማዕዘን ምት በሚመታበት ወቅት ኳሱን ለማግኘት የሞከረው የወልቂጤው 5 ቁጥር ዮናስ በርታ ከቶማስ ስምረቱ ጋር በጭንቅላቱ ተጋጭቶ በደረሰበት ጉዳት ጨዋታውን መቀጠል ባለመቻሉ ከሜዳ ተቀይሮ በመውጣት ለተጨማሪ የህክምና ዕርዳታ በአምፑላንስ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል ።

የመጀመሪያው ኢጋማሽ ጨዋታም ምንም ግብ ሳያስተናግድ 0 ለ 0 ተጠናቀቀ ።

የሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ በኋላ ባሉት የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ እንደ ወልቂጤ ከተማዎች በተሻለ ኳሱን በመያዝ ወደ ግብ ለመድረስ ጥረት ያደረጉ ሲሆን በአዳማ ከተማ በኩል የሚገኙ ኳሶችን በፍጥነት ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ለመድረስ ቢሞክሩም የወልቂጤ ከተማን የተከላካይ መስመር ያን ያህል የፈተኑ አልነበሩም ። 59ኛ ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር ላይ ጌታነህ ከበደ ያሻማውን የቅጣት ምት ተቀይሮ የገባው የአዳማ ከተማው ዮሐንስ ዮሴፍ ዮሐንስ በጭንቅላቱ ጨርፎ በራሱ ላይ አስቆጠረ ።
አዳማ ከተማ 0 – 1 ወልቂጤ ከተማ ።

ከግቧ መቆጠር በኋላ የፋሲል ተካልኝ ተጫዋቾች ቀደም ብሎ ካሳዩት እንቅስቃሴ በተሻለ ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት ያደረጉ ሲሆን 78ኛ ደቂቃ ላይም ኤልያስ ማሞ ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ ሚሊዮን ሰለሞን በግንባሩ በመግጨት ግብ አስቆጠረ ።

አዳማ ከተማ 1 – 1 ወልቂጤ ከተማ ። መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ተጠናቆ በተጨመረው 4 ደቂቃ ላይ የብሄራዊ ቡድኑ እና የወልቂጤ ከተማ የግራ መስመር ተከላካይ ረመዳን የሱፍ በሁለተኛ የቢጫ ካርድ ከሜዳ ሊወጣ ችሏል ።

የተጨመረው 4 ደቂቃ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሴኮንዶች በቀሩ ጊዜ የአዳማ ከተማው አብዲሳ ጀማል ከወልቂጤ ከተማው ግብ ጠባቂ ሲልቭያን ግቦሆ ጋር ተገናኝቶ የሳተው ኳስ አዳማ ከተማዎችን በእጅጉ ያስቆጨ ወልቂጤ ከተማዎችን ደሞ ከሽንፈት የታደገ ነበር ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...