መነሻ ገጽ አትሌቲክስ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ ክስ የመሰረቱት እነ ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ለዕርቅ ዝግጁ ነን አሉ….
አትሌቲክስኦሎምፒክ ኮሚቴየኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ

በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ ክስ የመሰረቱት እነ ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ ለዕርቅ ዝግጁ ነን አሉ….

አጋራ
አጋራ

*… የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ግን ፕሬዝዳንቱ ከውጪ ይምጡና አቋማችንን እናሳውቃለን ብሏል….

 

በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ ክስ የመሰረቱት እነ ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴ የተፈጠረውን አለመግባባት በዕርቅ ለመጨረስ ከፍርድቤት የቀረበላቸውን ጥያቄ መቀበላቸው ተሰማ።

ትላንት ጉዳኑን የያዘው ችሎት ፊት የቀረቡት ሁለቱ ወገኖች ፍርደ ቤቱ የተፈጠረውን አለመግባባት በዕርቅ እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሲሆን ከሳሾችና ጠበቆቻቸው በዕርቅ ለመስማማት ፍቃደኛ መሆናቸውን ለችሎቱ ገልጸዋል።

የተከሳሹ የኢትየጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጠበቆች በበኩላቸው ዕርቁን እንደሚደግፉት ነገር ግን የኦሎምፒክ ኮሚቴው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር
ወ/ጊዮርጊስ ሀገር ውስጥ ስለሌሉ ወደ ሀገር ሲመለሱ ከተወያዩበት በኋላ ውሳኔያቸውን እንደሚያሳውቁ የመደበኛ ፍርድቤቱ የህጋዊ ክርክሩ ሂደት ግን እንዲቀጥል ለችሎቱ መጠየቃቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ቴኒስና ቦክስ ፌዴሬሽኖች ከሻለቃ ሃይሌ
ገ/ስላሴና አትሌት ገዛኧኝ አበራ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ ባቀረቡት ክስ ተላልፎ የነበረው የአመራሮች የጉዞ ዕግድና የኦሎምፒክ ኮሚቴው የአካውንት ዕገዳ ተነስቶ የኦሎምፒክ ኮሚቴው የዕለት ተዕለት ስራ መቀጠሉንም ከታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
አትሌቲክስዜናዎች

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በዶፒንግ ምርመራ በቋንቋ ችግር ለሁለት ዓመታት እገዳ ተጣለባት!

ኢትዮጵያዊቷ የመካከለኛ ርቀት ሯጭ አትሌት ድሪቤ ዌልቴጂ የአደንዛዥ ዕፅ ምርመራ ባለማድረጓ ለሁለት...

አትሌቲክስዜናዎች

ትዕግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን አሸነፈች

በ45ኛው የለንደን ማራቶን የሴቶች ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ በ2:15:50 በቀዳሚነት አጠናቃለች። አትሌቷ...

አትሌቲክስዜናዎችየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

የአትሌቲክሱ አውራ ለመሆን 6 ዕጩዎች ተፋጠዋል…..

*.... የክልልሎችን ውክልናና ድጋፍ ይጠበቃል.... *.... ከበርካታ አመታት በኋላ የተደረገ ምርጫ ይሆናል....ብቸኛ...