By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የአትሌቲክሱ አውራ ለመሆን 6 ዕጩዎች ተፋጠዋል…..
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
መቻል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንአትሌቲክስ

የአትሌቲክሱ አውራ ለመሆን 6 ዕጩዎች ተፋጠዋል…..

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 1 year ago
Share
SHARE

*…. የክልልሎችን ውክልናና ድጋፍ ይጠበቃል….
*…. ከበርካታ አመታት በኋላ የተደረገ ምርጫ
ይሆናል….ብቸኛ ዕጩ የለም…..
*….. ከዕጩዎቹ ጀርባ ድጋፍ ሰጪ ሃይል ይጠበቃል..
*….. ለፍልሚያው ስካይ ላይት ተመርጧል…..
*…. ብሄራዊ ቡድኑን ዳግም ገንብቶ ከማናጀሮች መዳፍ የሚያስመልስ ፕሬዝዳንት ይጠበቃል…

በመጪው ታህሳስ ወር የሚካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ገና ከአሁኑ ትኩረት ስቧል።

ከታማኝ ምንጮች በተገኘ መረጃ በእግርኳሱ ምርጫ ላይ ይታይ የነበረውን የምረጡኝ ዘመቻን ብዙ ጊዜ በርካታ ሰዎች በማይወዳደሩበት አትሌቲክሱ ለመከሰት አትሌት ስለሺ ስህን ፣ አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማሪያም ፣ አትሌት መሰረት ደፋር ፣ አትሌት አሰፋ መዝገቡ፣ አቶ ጌታ ዘሩና አቶ ቢኒያም ምሩጽ የረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የስልጣን በትርን ለመረከብና የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን አትሌቲክስን ለመምራት ትልቅ ፍጥጫ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። አንዳንድ መረጃዎች ቁጥራቸው ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ይገልጻሉ።

ባለፉት አራት አመታት ፌዴሬሽኑን የመራችው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ያሸነፈችውን ምርጫ ጨምሮ ወደ ኋላ የተካሄዱት ምርጫዎች ውድድር ያልነበረባቸውና ከጀርባ ባሉ አካሄዶች የሚጠናቀቁ ምርጫዎች እንደነበሩ ይታወቃል። የዘንድሮ ግን የምረጡኝ ግብግቦች የሚታዩበት ከመጋረጃ ጀርባ ምክክሮች የሚኖሩባቸው ፖለቲካዊ አመራሮች፣ ባለሀብቶች ፣ ታዋቂ ሰዎች ተጽዕኖ ፈጠሪዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸውን የሚያስገቡበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

- ማሰታውቂያ -

የቶኪዮው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሊካሄድ ወራቶች በቀሩበት በአሁኑ ወቅት የሚመረጠው ፕሬዝዳንት ስፖርቱን የማረጋጋት የአትሌቶችን ስነልቦና የሚደግፍ ስራ መስራት ፣ ብሄራዊ ቡድኑን ዳግም መመስረትና የማናጀሮችን እጅ መመለስ ከምንም በላይ በየትኛውም አቅጣጫ የማይጎተት ለአንድ አላማ የቆየ የስራ አስወጻሚ ኮሚቴ ውህደት መፍጠር አትሌቲክሱን ከዘርና ከሃይማኖት ልዩነት ማጽዳት የሚጠበቅበት ሆኗል።

በፓሪስ ኦሎምፒክ የተገኘውን ደካማ ውጤት ተከትሎ እንደ ዋና ችግር ከታዩት ምክንያቶች መሃል ዋናው የብሄራዊ ቡድን መፍረስ ሲሆን ይህን የማስተካከልና ቡድኑን ዳግም የመመለስ የማናጀሮች አሰልጣኞችና የአትሌቶች ባሎች ከፍተኛ ጫና የሚወገድበት ሁኔታን የመፍጠርና አትሌቲክሱን የማዳን ትልቅ ሃይል የሚይዝ ፕሬዝዳንትና ስራ አስፈጻሚ የሚመረጥበት እንዲሆን የመምረጫ ካርዱን የያዙ ተወካዮች ትልቅ ሀገራዊ ሃላፊነት እንደሚሆን የብዙዎችም እምነት ሆኗል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው ታህሳስ ወር በስካይላይት ሆቴል ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ተጥሎ የነበረው የውጪ ጉዞ ዕገዳ ተነሳ
Next Article ፋሲል ተከላካይ አስፈርሟል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
Uncategorized

የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ኘሮግራም

hatricksport team By hatricksport team 9 years ago
መቐለ 70 እንደርታ ከናይጀርያዊው ተከላካይ ጋር ተለያይቷል
ቅደመ ጨዋታ ዳሰሳ | የቶታል ካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ቅ/ጊዮርጊስ ከ ኬሲሲኤ
ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የማጠቃለያ  የዋንጫ  ጨዋታ  በቀጥታ /LIVESCORE/
“የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት አያስደነግጠንም፤ በገንቢነቱ ነው የምንወስደው”አቶ ወንድምኩን አላዩ (የኢ.ፉ.ፌ የፅ/ቤት ኃላፊ)
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
Welcome Back!

Sign in to your account

Lost your password?