The Midfield Maestro

በይስሐቅ በላይ
በግብፅ የሚገኝ Kinfut ድረ ገፅ በግብፅ ሊግ ከሚጫወቱ ግን ደግሞ ወደ አውሮፓ ተዛውረው የመጫወት ትልቅ አቅም ካላቸው
ምርጥ 10 ተጨዋቾቹ ዝርዝር ውስጥ የኢትዮጵያዊው ሽመልስ በቀለን ስም በ5ተኛ ደረጃ አስቀምጦታል፡፡ እንደ ድረ ገፁ ዘገባ
ከሆነ ሽመልስ በቀለ ካሉት ደካማ ጎኖቹ አንደኛው ያለውን አቅም አውጥቶ ወደ አውሮፓ ሄዶ አለመጫወቱ ነው ሲል ድረ ገፁ ከፍ
አድርጎ አወድሶታል፡፡
የላቀ ጥበብ (Skills) ባለቤት፣ የአሲስት (Assist) ንጉስና ግብ አነፍናፊው ሽመልስ በቀለ ከሐዋሳ ከተማ
የተነሳው የእግር ኳስ ህይወቱ ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ ተሻግሮ የፕሮፌሽናልነት ህይወቱ
ለአመታት እየመራ ይገኛል፡፡ ከሀዋሳ፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለኢትሃድ ትሪፖሊ፣ ለአልሜሪክና ከ2014 ጀምሮ
ለግብፁ ፔትሮጄት በመጫወት ላይ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ በድንቅ ችሎታው በግብፅ ሊግ ከፍተኛ ክብርና
አመኔታ ከሚሰጣታቸው ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም በቅቷል፡፡
በግብፅ የተሳኩ አመታትን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የመሀል ሜዳው ቴክኒሺያን ሽመልስ በቀለ የግብፁ
ፔትሮጄት አምበል በመሆን ከሀገር ውጪ የሚገኝ ክለብን በአምበልነት የመራ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ
ተጨዋች ለመሆንም በቅቷል፡፡
“ኢትዮጵያዊኖች በግብፅ ሊግ ከፍተኛ ተቀባይነትን እያገኙ ነው” የሚለው ሽመልስ በቀለ ጌዶ ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ግድብ ዙሪያ
የጎሪጥ የምትተያየው ግብፅ በተለይ የካይሮ ከተማ “ኑሮ ተስማምቶኛል ሊጉም ተመችቶኛል” በማለትም ይናገራል፡፡ በ2018/19 የግብፅ
ሊግ በግብ አግቢዎች የመጀመሪያው ረድፍ ላይ በስድስት ጎሎች ስሙን ማስፈር የቻለው ሽመልስ “ከዚህ በግብፅ የሚገኝ Kinfut ድረ ገፅ በግብፅ ሊግ ከሚጫወቱ ግን ደግሞ ወደ አውሮፓ ተዛውረው የመጫወት ትልቅ አቅም ካላቸው
ምርጥ 10 ተጨዋቾቹ ዝርዝር ውስጥ የኢትዮጵያዊው ሽመልስ በቀለን ስም በ5ተኛ ደረጃ አስቀምጦታል፡፡ እንደ ድረ ገፁ ዘገባ
ከሆነ ሽመልስ በቀለ ካሉት ደካማ ጎኖቹ አንደኛው ያለውን አቅም አውጥቶ ወደ አውሮፓ ሄዶ አለመጫወቱ ነው ሲል ድረ ገፁ ከፍ
አድርጎ አወድሶታል፡፡
የላቀ ጥበብ (Skills) ባለቤት፣ የአሲስት (Assist) ንጉስና ግብ አነፍናፊው ሽመልስ በቀለ ከሐዋሳ ከተማ
የተነሳው የእግር ኳስ ህይወቱ ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ ተሻግሮ የፕሮፌሽናልነት ህይወቱ
ለአመታት እየመራ ይገኛል፡፡ ከሀዋሳ፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለኢትሃድ ትሪፖሊ፣ ለአልሜሪክና ከ2014 ጀምሮ
ለግብፁ ፔትሮጄት በመጫወት ላይ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ በድንቅ ችሎታው በግብፅ ሊግ ከፍተኛ ክብርና
አመኔታ ከሚሰጣታቸው ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም በቅቷል፡፡
በግብፅ የተሳኩ አመታትን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የመሀል ሜዳው ቴክኒሺያን ሽመልስ በቀለ የግብፁ
ፔትሮጄት አምበል በመሆን ከሀገር ውጪ የሚገኝ ክለብን በአምበልነት የመራ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ
ተጨዋች ለመሆንም በቅቷል፡፡
“ኢትዮጵያዊኖች በግብፅ ሊግ ከፍተኛ ተቀባይነትን እያገኙ ነው” የሚለው ሽመልስ በቀለ ጌዶ ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ግድብ ዙሪያ
የጎሪጥ የምትተያየው ግብፅ በተለይ የካይሮ ከተማ “ኑሮ ተስማምቶኛል ሊጉም ተመችቶኛል” በማለትም ይናገራል፡፡ በ2018/19 የግብፅ
ሊግ በግብ አግቢዎች የመጀመሪያው ረድፍ ላይ በስድስት ጎሎች ስሙን ማስፈር የቻለው ሽመልስ “ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጎሎችን
ማስቆጠር ከቻልኩ በፔትሮጄት አዲስ ታሪክ አፅፋለሁ” ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ብ/ቡድን በካሳራኒ ከኬንያ አቻው ጋር ላለበት የመልስ ጨዋታ ወደ ናይሮቢ ለመብረር ሰዓታት በቀሩበት ወቅት በድንገት
በካፒታል ሆቴል የገኘው የሀትሪክ ጋዜጣ ማኔጅንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ለጉዞ በመጣደፍ ላይ የሚገኘውን
ብዙ ከመናገር ቁጥብ የሆነውን ሽመልስ በቀለን የተጣበበ ጊዜውን ተሻምቶ በግል ህይወቱ፣ ስለሚጫወትለት የግብፁ ፔትሮጄት፣
አብሮት ባለመጫወቱ ስለሚቆጨውና ስለሚያደንቀው ተጨዋችና ሌሎች ጉዳዮችን በማንሣት አነጋግሮታል “ከሽመልስ ጋር የነበረው
ቆይታ ከእሁዱ የኬንያ 3ለ0 ሽንፈት በፊት በእለተ ሐሙስ የተደረገ ቃለ ምልልስ እንደሆነ ለአንባቢዎቻችን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
አብሮት ባለመጫወቱ ስለሚቆጨውና ስለሚያደንቀው ተጨዋችና ሌሎች ጉዳዮችን በማንሣት አነጋግሮታል “ከሽመልስ ጋር የነበረው
ቆይታ ከእሁዱ የኬንያ 3ለ0 ሽንፈት በፊት በእለተ ሐሙስ የተደረገ ቃለ ምልልስ እንደሆነ ለአንባቢዎቻችን በአ
የሚያሸከረክረው መኪና
“ለዕይታ ሳቢና የዘመኑን ቴክኖሎጂ
የተጠቀመ NISSAN JUKE
ምን ማድረግ ደስታን ይሰጠዋል

“መልካም ነገር ለሰዎች ማድረግ
ደስታን ይሰጠኛል፤ መልካም ነገር ማድረግ
ኃይማኖታዊም ሰዋዊም ትልቅ ትርፉን
ያስገኛል፤ ስለዚህ ለሰዎች መልካም ማድረግና
መልካም ነገር መስራት ያስደስተኛል፡፡
አዘወትሮ የሚለብሰው
“አለባበስ ላይ በጣም በተለየ የምለው ነገር
የለም፤ ከሰውነቴ ጋር የሚስማማኝን ሁሉ
እለብሳለሁ፡፡ በአብዛኛው ግን ቲ ሸርት በቱታ
ስለብስ ቀለል ያለ ስሜት ይሰማኛል”
ብዙ ገንዘብ የሚያስወጣው
“Shopping (ገበያ) ስወጣ ብዙ ገንዘብ
እጨርሳለሁ፤ የወደድኩትን ዕቃ ለመግዛት
አልሰስትም፡፡ በአጭሩ አንዴ Shopping
(ገበያ) አልውጣ ከወጣሁ ብዙ ገንዘብ
እጨርሳለሁ፡፡
እድል ቀንቶኝ አንዴ አግኝቼ ባዋራው
የሚለው የዓለማችን ታላቅ ሰው
“የጥበበኛና ተዓምረኛ እግር ባለቤት
የሆነው ሮናልዲንሆ ጎቾ፤ እድል ቀንቶኝ
ሮናልዲንሆን ባገኘውና ባወራው በጣም
እደሰት ነበር፡፡ ከእሱ ጋር በሚኖረኝ አጭር
ቆይታም ስለ ጥበበኛ እግሮቹ አወራው ነበር፡፡”
በክለብ ደረጃ ድጋፍን ያለስስት የሚስጠው
የውጪ ቡድን
“ፔትሮጄት እና ፔትሮጄትን ብቻ፤
ከክለቤ ውጪ ማንን ያደንቃል ብለህ ጠብቀህ
ነው?
ከአለማችን ታላላቅ አሰልጣኞች የተለየ
ክብርና ቦታ የምትሰጠው?
“ለማንቸስተር ዩናይትዱ ታላቅ ሰው
ለሰር አሌክስ ፈርጉሰን የተለየና ትልቅ ቦታ
አለኝ፤ፈርጉሰን የውጤትና ጥሩ ጨዋታን
የሚጫወት ቡድን የሚገነቡ የዩናይትድ ብቻ
ሣይሆን የእግር ኳሱም ትልቅ ምልክት የሆኑ
አልጣኝ በመሆናቸው ለእሳቸው የተለየ ቦታ
አለኝ፡፡”
የሚጠቀመው
የእጅ ስልክ(ሞባይል)
“I phone 8
plus

አጥብቆ የሚጠላው ነገር
“ውይ…!
ወሬና ወሬኛ ሰው
አልወድም፤ ከዚህ
ውጪ በሰው ህይወት
ውስጥ የሚገባ፣
ወሬ ከወዲያ ወዲህ
የሚያመላልስ ሰው
ብዙም አይመቸኝም፡፡”
ሀትሪክ፡- ሽሜ
ወደ ኬንያ ለመጓዝ
እየተዘጋጀህ ባለህበት ሰዓት
ቀላል ልምምድህን አቋርጠህ
ለጋዜጣችንና ለአንባቢዎቻችን ክብር
ሰጥተህ ለቃለ-ምልልሱ ስለተባበርከኝ ከልብ
አመሰግናለሁ፡፡
ሽመልስ፡ እኔም ስለጋበዛችሁኝ
አመሰግናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ሽሜ ካለፉት ጥቂት አመታት
ወዲህ በአብዛኛው ኑሮህም በክለብ ደረጃ
የምትጫወትበት ሀገርም ግብፅ ሆናለች፤
ግብፅ ተመችታሀለች ልበል…?
ሽመልስ፡ እንዳልከው በግብፅ እንደቀልድ
ረዘም ያሉ ዓመታትን አሳልፌያለሁ፤
ግብፅ ተመችታኛለች፣ ተቀብላኛለች ማለት
ይቀለኛል፡፡
ሀትሪክ፡-የምትጫወትበት ክለብ የግብፁ
ፔትሮጄት መቀመጫ ሱዝ ነው በሱዝ
ህይወትን እንዴት እየመራህ ነው…?
ሽመልስ፡ እንዳልከው የፔትሮጄት
መቀመጫ ሱዝ ነው፤ እኔ ግን በአብዛኛው
የምኖረው በዋና ከተማዋ በካይሮ ነው፡፡ ሱዝ
የክለቡ ስታዲየም ያለበት ከተማ በመሆኑ
ጨዋታችንን የምናደርገው እዛ ነው፤ ልምምድ
የምናደርገው ግን ካይሮ ነው፡፡ ጨዋታ ሲኖረን
ወደ ሱዝ እንሄዳለን፤ በአጭሩ ሁለቱም ጋ
ተመችቶኝ ነው እየሠሩ ያለሁት፡፡

ሀትሪክ፡-ለፔትሮጄት ፊርማህን ካኖርክ
ድፍን አራት አመት ሞላህ ልበል? የክለቡ
ቆይታህን እንዴት ትገልፀዋለህ…?
ሽመልስ፡- በሚገርምህ ሁኔታ
ፔትሮጄትን ከተቀላቀልኩ አሁን አምስተኛ
አመቴን ይዣለሁ፤ በክለቡ በጣም ደስተኛ
ከመሆኔ የተነሣ አምስቱ አመት የአምስት
ቀን ያህል ሣይታወቀኝ ነው ያለፈው፡፡
በእግር ኳስ ህይወቴም ረዥም ጊዜ የቆየሁት
ወይም ያሳለፍኩበት ክለብ በፔትሮጄት
ውስጥ መሆኑን ስታይ በእርግጥም ክለቡ
እንደተስማማኝ በደስታ የተሞሉ ጊዜያትን
እያሳለፍኩ እንደሆነ በቀላሉ ትረዳለህ፡፡
ሀትሪክ፡- ለክለቡ በፕሮፌሽናልነት
ከመጫወት አልፈህ በግብፅ ብቻ ሣይሆን
በሌላም ሀገር ከኢትዮጵያ ሄደህ የአምበልነት
ማዕረግን ያገኘህ ተጨዋች ለመሆን በቅተሃል…
ይሄ ምን ስሜት ይፈጥርብሃል…?
ሽመልስ፡- በጣም ደስታም ኩራትም
ይሰማኛል፤ ምክንያቱም ክለቡ በእኔ ላይ
ያለውን እምነትና ለእኔ ያለውን ክብር
በተግባር የሚያሳይ ነው፡፡ አሁን ባለው
ዘመናዊ እግር ኳስ አምበል ማለት ተጨዋችን
ከአሰልጣኝ፣ ተጨዋቾችን ከክለቡ አመራሮች
ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው፡፡ የተጨዋቾች
ድምፅም በመሆን የሚያገለግል ነው፡፡ ከዚህ
አንፃር አምበል በመሆኔ ትልቅ ኃላፊነትም
እንደተሰጠኝ ነው የማስበው፤ክለቡ ለዚህ
ክብር እንድበቃ በማድረጉም በጣም ደስተኛ
መሆኔን ነው የምገልፀው፡፡
ሀትሪክ፡- የአንተ በግብፅ ሊግ ከመጫወት
አልፎ የቡድኑ አምበል እስከመሆን መድረስ
ግብፃዊያን በኢትዮጵያዊያን ተጨዋቾች ላይ
ከፍተኛ እምነት እያሳደሩ መምጣታቸውን
ያሳያል ብሎ ማሰብ ይቻላል…?
ሽመልስ፡- ይሄንን አትጠራጠር፤
ኢትዮጵያኖች በግብፅ በጣም ተቀባይነትና
ክብር አላቸው፡፡ ከእኔ ውጪ ዑመድንና ጋቶች
ፓኖምን ብትወስድ በግብፅ ትልቅ ተቀባይነትና
ክብር አላቸው፤ የተሻለ እንቅስቃሴ
ስለሚያሳዩ እምነት እንዲጥሉባቸው
ግብጾችን አሰገድደዋል፡፡ አቅም ካለህ እምነት
የማይጣልበት ምንም ምክንያት አይኖርም፡፡
የሀገራቸው ዜጋ እያለ ለእኔ የአምበልነቱን
ክብር የሰጡኝ እምነትም ክብርም ስላላቸው
ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ስታያቸው ግብጾች
ለኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ትልቅ ክብርም
እምነትም አላቸው፡፡
ሀትሪክ፡- ሽሜ ያለቀላቸው ኳሶችን
ከማቀበል ስራህ ውጪ ግብ አግቢ ሆነሃል፤
በግብፅ ሊግ ዘንድሮ በሽመልስ በቀለ ስም
የተመዘገቡ ስንት ጎሎች አሉ…?
ሽመልስ፡- እስከአሁን ባለው ሁኔታ
ስድስት ግቦች በስሜ ተመዝግበዋል፤ በእነዚህ
ግቦችም የኮከብ ግብ አግቢነቱን መሪነት
ከዛማሌኩ አላ እና ከኤል ዳካሂልያው ሳላማ
ጋር በጋራ እየመራን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ
ተጨማሪ ጎሎችን እያስቆጠርኩ የምሄድ
ከሆነ የአዲስ ታሪክ ባለቤትም የምሆን
ይመስለኛል…ሣቅ…
ሀትሪክ፡- …የአዲስ ታሪክ… ባለቤት…
ስትል… ?
ሽመልስ፡- …እንዳልኩህ እስከአሁን
ስድስት ግቦችን አስቆጥሬያለሁ፤ ከዚህ በኋላ
ሶስት ጎልና ከዚያ በላይ የማገባ ከሆነ የክለቡ
የምንጊዜውም የግብ አግቢነት ክብር ባለቤት
እሆናለሁ፤ይሄ ለእኔም ለክለቡም አዲስ ታሪክ
ነው የሚሆነው፡፡
ሀትሪክ፡- …ይሄን… አዲስ ታሪክ…
ለማፃፍ… ተዘጋጅተሃል…? የሚሳካስ
ይመስልሃል…?
ሽመልስ፡-…እስከአሁን… ያደረግነው…
ስምንት ጨዋታ ነው፤… በስምንት ጨዋታ
ስድስት ጎሎችን አስቆጥሬያለሁ፤ ከዚህ በፊት
ይሄን ያህል ጎል ገና በ8 ጨዋታ አስቆጥሬ
አላውቅም፤ ባስቆጥር በአመት አራት ወይም
ስድስት ጎል ብቻ ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር ስታየው
ገና በ8 ጨዋታ የተሻለ ግብ አለኝ፤ ከሚቀረን
ጨዋታ አንፃር ሶስትና ከዚያ በላይ ጎል
ማስቆጠር ከባድ ይሆንብኛል ብዬ አላስብም፤
ያንን ማድረግ ከቻልኩ ወደ አዲስ የክለቡ
ታሪክ እሄዳለሁ ማለት ነው፡፡
ሀትሪክ፡-…ሽምዬ …ይሳካልህ…
እንደምኞትህም…ይሁንልህ.፤ካስቆጠርኳቸው
ግቦች የእኔ ምርጡ ነው ብለህ የምታዳላለት
ግብህ የትኛው ነው…?
ሽመልስ፡- ፔትሮጄትን እንደተቀላቀልኩ
በመጀመሪያ አመት ከ….. ጋር ስንጫወት
ከሩቅ ሹት መትቼ ያስቆጠርኩት ግብና
ባለፈው አመት ደግሞ ከእነ ዑመድ ኡከሪ
ቡድን ጋር ስንጫወት ላስቆጠርኳቸው ሁለት
ግቦች የተለየ ቦታ የምሰጣቸው ናቸው፡፡

ሀትሪክ፡- የክለብህ የቅርብ ጓደኞና ክፍል
የምትጋራው ተጫዋች ማነው…?
ሽመልስ፡- ዞላ ይባላል፣ ከእሱ ጋር በጣም
እንቀራረባለን እንግባባለን፤ ሀትስና ዞላ ጋር
በጣም ቅርበት አለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ክለብህ ፔትሮጄት በአሁኑ
ሰዓት በ14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ይህ መሆኑ
ከክለብህ ጋር ዋንጫ የማንሣት ህልምህን
ያጨልመዋል…?
ሽመልስ፡- የምናወራው እውነት ከሆነ
ዋንጫ የማንሣት እድሉ አለን ብዬ ለመናገር
ይቸግረኛል፤ገና ቀሪ ጨዋታዎች ስላሉ
ቢያንስ የተሻለ ደረጃ ማለትም ከ1-6 ውስጥ
ባለው ደረጃ ውስጥ ገብተን የአመቱን ውድድር
ልናጠናቅቅ እንችላለን የሚል እምነት ነው
ያለኝ፡፡ አሁን ያለንበት ደረጃ ሩቅ ቢመስልም
ውጤቱ ብዙም ልዩነት የለውም ተቀራራቢ
ነው፤ በተለይ ከ5ኛ-12ኛ ያሉት የአንድና
የሁለት ጨዋታ ውጤት ልዩነት ነው ያላቸው፡
፡ ከዚህ አንፃር ዋንጫው ቢቀርም የተሻለ
ደረጃ ይዘን እናጠናቅቃለን ብዬ አስባለሁ።
ለክለቡ አምስት አመት እንደተጫወተ ክለቡን
በአምበልነት እንደመራ ሰው ከፔትሮጄት ጋር
ያለኝ ኮንትራት ከመጠናቀቁ በፊት አንድ
ትልቅ ታሪክ የማፃፍ እድሉ ቢኖረኝ የበለጠ
ደስ ይለኝ ነበር፡፡
ሀትሪክ፡-ደሞዝ ስንት ይከፍሉሃል
የሚለው ጥያቄ ብዙ ተጨዋቾችን
እንደማያስደስት አውቃለሁ፤ አንተ ግን
በዚህ በኩል ችግር የለብህም ብዬ ስለማምን
በፔትሮጄት በወር ስንት ብር ይቆርጥልሃል…?
ሌሎች የምታገኛቸው ጥቅማጥቅሞችስ…?
ብዬ ብጠይቅህ እንደማታሳፍረኝ ተስፋ
አደርጋለሁ…?
ሽመልስ፡…. ሣቅ… የማገኘውን ደሞዝ
ብነግርህ አይጠቅምህም፤ ስምምነታችን
በኮንትራት ስለሆነና ስፈርም አንዴ
ስለምቀበልና ስለምወስድ እንደዚህ ነው
የማገኘው ለማለት ይቸግረኛል፡፡ ከዚህ
ውጪ ክለቡ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን
ይሰጠኛል፤ፕሮፌሽናል ክለብ ስለሆነ
አስፈላጊውን ነገር አማልተውልኛል፤ ቤትም
የተከራዩልኝ እነሱም ናቸው፡፡ በአጠቃላይ
በጣም ጥሩ ተጠቃሚ ነኝ የሚለውን
ብትወስደው ደስ ይለኛል፡፡
ሀትሪክ፡-በግብፅ ቆይታህ የባህል ግጭትClash) ወይም ተፅዕኖስ አልገጠመህም… ?
ሽመልስ፡ መጀመሪያ ላይ ለሀገሩም
ለባህሉም እንግዳ ስለነበርኩ መጠነኛ ችግር፣
ትንሽ ግር የማለት ነገር ገጥሞኝ ነበር፡፡
አሁን ግን ነዋሪ ሆንኩ እኮ… አምስት አመት
ሞላኝ…ሣቅ… ከዚህ አንፃር ሁሉንም ነገር
ለምጄዋለሁ፡፡ የከበደኝ ወይም የተቸገርኩበት
ነገር የለም፡፡
ሀትሪክ፡-…ለምሣሌ አመጋገብ ላይ…?
…እዚህ ከለመድከው… አንፃር ማለቴ ነው…?
ሽመልስ፡-…አመጋገብን በተመለከተ…
ያው እንደ ሀገር ቤት እንደማይሆን ግልፅ
ነው፤ …እዚህ የለመድከውን ነገር… ሙሉ
በሙሉ አትጠብቅም…፤ ያም ቢሆን ግን…
በዚህ በኩል… ክፍተት… እንዳይገጥመኝና…
እንዳልቸገር… በማሰብ ራሴ ኩክ እያደርኩ
(አብስዬ) እመገባለሁ…፤ራሴ ምግቦችን
አብስዬ መመገቤ በዚህ በኩል በሚፈጠር
ችግር እንዳልጎዳ አድርጎኛል፡፡

ሀትሪክ፡-… እንዴ ሽሜ…የተዋጣልህ
ሼፍ ሆነሃላ…?… ለምሣሌ ምን አይነት
ምግብን አጣፍጦ በመስራት… ይዋጣልኛል
ትላለሀ…?
ሽመልስ፡-…ሣቅ… ያን ያህል ባለሙያ ነኝ
ባልልም… ለራሴ የሚሆን ነገር… አጣፍጬ..
ሠርቼ.. እመገባለሁ…፡፡ …በዚህ በኩል…
በተለይ ራሴን… መገንባት ስለምፈልግ… ጣት
የሚያስቆረጥም… የቡላ ገንፎ… ሠርቼ…
አዘውትሬ እመገባለሁ…፡፡(ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …በግብፅ… ረዥም አመት…
አስቆጥረሃል… ከዚህ አንፃር… ከግብጾች
ምግብ… የተመቸህና አዘውትረህ…
የምትመገበው… ለየት… ያለ ባህላዊ…
ምግብስ አለ…?
ሽመልስ፡- … የሚገርምህ… ግብጾች…
የተለየ የምትለው… ባህላዊ ምግብ…
የላቸውም፤ ባህላዊ… ወይም… አዘውትረው…
የሚመገቡት… ሩዝን ነው…፡፡ …በአብዛኛው
ግብፃዊያን የሚመገቡት ሩዝን ነው ማለት
እችላለሁ፤… እኔም አልፎ አልፎ… ሩዝን
ነው የምመገበው…፡፡
ሀትሪክ፡-…በግብፅ የሚጫወቱ…
ኢትዮጵያውያን… ተጨዋቾች ቁጥር…
እየጨመረ ነው፤ዑመድ አለ… ጋቶች አለ…
አንተ አለህ… እርስበርስ… እየተገናኛችሁ
የምትጫወቱበት… ዘና ፈታ… የምትሉበት
አጋጣሚ… አለ… ?
ሽመልስ፡- …ያለንበት ቦታ… የተለያየ…
በመሆኑ… ለጨዋታ ስንገናኝ… ካልሆነ…
በስተቀር… የመገናኘት እድሉ… ብዙም
የለም…፤… ባንገናኝም ግን… ብዙውን ጊዜ…
እንደዋላለን…፤ ለጨዋታ ስንገናኝ… ግን…
ባገኘነው… አጋጣሚ… እንጨዋወታለን…
እናወራለን፡፡… እኔ ያለሁት ካይሮ…
እነሱ… ሌላ ቦታ… መሆናቸው… በአካል
የመገናኘት… እድሉን አጥብቦታል…፡፡
ሀትሪክ፡-…በግብፅ ከጨዋታና
ከልምምድ… ውጪ… ያለውን ጊዜ… በምን
ታሳልፋለህ…?
ሽመልስ፡-…በመተኛት (በቂ እረፍት
በመውሰድ)…፣ …ፊልም በማየት…፣ …
አንዳንዴ ደግሞ… ሾፒንግ በመውጣት
(በመገበያየት)… የማገኛትን… ትርፍ
ጊዜ… አሳልፋለሁ…፡፡ …በአብዛኛው ግን…
ልምምድና… ጨዋታ ስላለ… ብዙም…
ትርፍ የሚባል… ጊዜ… የለኝም….፡፡
ሀትሪክ፡-…የግብፅ ሊግ… አሁንም…
የሁለት ፈረሶች… ግልቢያ ነው…፤
የዛማሌክና የአል-አህሊ… የበላይነት…
ጎልቶ የሚታይበት… እንደሆነ ነው…
የሚታወቀው…፡፡ …ይሄ የበላይነት
(Domination)…አሁንም…. እንደቀጠለ
ነው… ማለት እንችላለን…?
ሽመልስ፡- …አዎን… አሁንም
እንደዛው… ነው… ማለት ይቻላል…፤…
ሁልጊዜ… ከደረጃ ሰንጠረዡ… አናት
ላይና… ከሻምፒዮናነቱ ጋር… ስማቸው…
በአብዛኛው… የሚነሣው … እነዚህ… ሁለት
ክለቦች… የሀገሪቱን ሊግ… በውጤታቸው
ተቆጣጥረውታል…፤… ፉክክሩም
የሚያዘነብለው በእነሱ ዙሪያ ነው፡፡
ሀትሪክ፡-…እንዳልከው… ዛማሊክ…
አሁንም… በደረጃው ሰንረጠዥ… አናት…
ላይ ቢሆንም… አል- አህሊ ግን… ተንሸራቶ…
8ኛ ደረጃ ላይ… ከመገኘቱ አንፃር… ፉክክሩ…
በሁለቱ… መሀል ነው… ማለት ይቻላል… ?
ሽመልስ፡- …አል-አህሊ… ወደ ታች
የወረደው… ቀሪ ጨዋታዎችን… ስላላደረገ
ነው…፤… ገና ቀሪ… ጨዋታዎች… አሉት…
የነጥብ ልዩነታቸው… እንደደረጃቸው…
አይደለም…፤ አንድና… ሁለት…
ጨዋታዎች… ሁሉንም ነገር… ይለወጣሉ፤
አሁን… ልዩነት ያለ… ቢመስልም… ዞሮ
ዞሮ… ፉክክሩም… የኃይል ሚዛኑም… ወደ
እነሱ… ማዘንበሉ… አይቀርም….፡፡
ሀትሪክ፡-…አንተ ከምትጫወትበት…
የግብፅ… ሊግና… ከኢትዮጵያ… ፕሪሚየር
ሊግ… የቱ… ይበልጣል?… ብልህ… መልስህ
ምንድነው…?
ሽመልስ፡ … (ሣቅ)… ሁለቱም…
የየራሣቸው ነገር… አላቸው፤…በግብፅ ሊግ…
የኳስ ክህሎት ብዙም አታይም… ፍላጎት
ግን… በጣም አላቸው…፤ በዚህም… በጣም
ይበልጡናል …በሊግ ደረጃም… ካየኸው…
ደረጃውን… የበጠቀ ሊግ… ስላላቸው
በዚህም… ይበልጡናል…፡፡
ሀትሪክ፡-የግብፅ ሊግ የሌላ ሀገር
ዜግነትያላቸው በረኞች በሊጉ እንዲጫወቱ
አይፈቅድም፤ በከፍተኛ የግብ ጠባቂ ድርቅ
እየተጠቃ ያለው እግር ኳሳችንና ሊጋችን
የውጪ ሀገር ግብ ጠባቂ እንዳይጫወት
የሚከለክለውን የግብፅ ሊግን ህግ ወደ ሀገር
ቤት አምጥተን ኮፒ ፔስት ብናደርገው የሚል
እምነት አለኝና አንተ ምን ትላለሀ…?
ሽመልስ፡ ቢሆን በጣም ነው ደስ
የሚለኝ፤የሀገራችን ክለቦች የውጪ ዜጋ
በሆኑ ግብ ጠባቂዎች ተጥለቅልቀዋል፤
ይሄ ደግሞ ግብ ጠባቂዎችን እንዳናፈራ በር
ይዘጋል፡፡ ግብጾች ይሄን ሕግ በማውጣታቸው
ተጠቃሚ ሆነዋል፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ
ጊዜ ተጠይቄ መልስ ሰጥቼበታለሁ፡፡ ይህንን
የግብፅ ተሞክሮ ወደ ሀገር ቤት በማምጣት
በግልፅ እየታየ ያለውን የግብ ጠባቂዎች ችግር
መቅረፍ ይችላል፡፡ የፌዴሬሽኑ አመራሮች
ትኩረት ቢሰጡት ተሞክሮው የግብ ጠባቂ
ችግር እንዲቀረፍ ለእግር ኳሱ እድገትም እገዛ
ስለሚያደርግ ቢታሰብበት ደስ ይለኛል፡፡
ሀትሪክ፡-…ከግብፅ ሌላ የምንማረው…
ወይም… የምንወስደው…አለ… ?
ሽመልስ፡ የግብ ጠባቂዎችን ከላይ ባለው
መልኩ ገልጫለሁ፤ የፕሮፌሽናል ተጨዋች
ቁጥርን በተመለከተ መቀነስ ቢቻል ለሀገራችን
ወጣቶች እድሉ በብዛት የሚሰጥበት
መንገድንም ብንከተል ነው የምለው፡፡
ሀትሪክ፡- …በአሁን ሰዓት… አንተ…
ሀገራችን ካሏቲ… ምርጥ አማካዮች… አንዱ..
ነህ.. በዚህ ቦታ ላይ እያደነክና… እያየኸው…
ያደከው… የእኔ… ምርጡ… አማካይ…
የምትለው …ማንን … ነው…?
ሽመልስ፡ …ሙሉጌታ ምህረትን…!
ሙሌ… ምርጥ… የአማካይ ችሎታን…
ከምርጥ ባህሪ… ጋር… የሰጠው…
ተጨዋች… በመሆኑ… እሱን እያየሁ ነው…
ያደኩት… የማደንቀውም… እሱን ነው…፡፡
ሀትሪክ፡-…ሽመልስ ከሀገር ቤት…
የወጣው… በደንብ ተጫውቶ… ሳይጠግብ
ነው… የሚሉ አሉ… ትስማማለህ…?
ሽመልስ፡ …እውነታውን… ስታየው…
በእግር ኳስ… ህይወቴ… ረዥም ዓመት…
የተጫወትኩበት… ክለብ… የግብፁ
ፔትሮጄት… መሆኑን ስታይ… የምትረዳው
ነገር አለ…፤ ብዙዎች… ሳትጠገብ ነው
የወጣኸው… ይሉኛል… እንግዲህ የእንጀራ
ጉዳይ…፣ የህይወት ጉዳይ… ሆኖ ወጥቼ…
የምጫወትበት እድል ተፈጥሯል…፡፡
ሀ ት ሪ ክ ፡ – … ሽ ሜ …
በሀገር ቤት… ያልተጠገበ
ተጨዋች… በመሆኑ… ተመልሶ
ሲጫወት… ብናየው… ብለው…
ለሚመኙስ… ምን ትላቸዋለህ…? …
አንተስ የመመለሱ ሃሳብ የለህም….?
ሽመልስ፡ …ወደፊት የሚሆነው ነገር
አይታወቅም… እኔም… ወደ ሀገሬ…
ተመልሼ ብጫወት አይከፋኝም…፤
ይበልጥ እደሰታለሁ…፡፡ …ግን… መቼ
ነው የሚሆነው…? …ቀኑን… ዛሬ ላይ
ሆኜ… በትክክል አላውቀውም …ወደፊት…
የምናየው ነው የሚሆነው…፡፡
ሀትሪክ፡- …ግን… የምትመለስ ከሆነ…
የማንን ማልያ… ለብሰህ…. ለመጫወት
ታስባለህ…?
ሽመልስ፡ …ይሄንንም… ዛሬ ላይ ሆኜ…
አላውቀውም… ያኔ… ሲሆን… በሰዓቱ
የሚወስንም… የሚታወቅም… ነገር ነው
የሚሆነው፤… አሁን ለጊዜው… የፔትሮጄት
ተጨዋች… መሆኔን ብቻ ነው የማውቀው…፡
፡ …ጊዜው… ሲደርስና ወደ ሀገር ቤት
ተመልሼ ለመጫወት ስወስን …ይሄንን ጥያቄ
ብትጠይቀኝ… ትክክለኛውን መልስ ልሰጥህ
እችላለሁ…፤… አሁን ባለው ሁኔታ ግን…
እንዲህ ነው… ማለት አልችልም…፡፡
ሀትሪክ፡-…የግብፅና… የሊቨርፑሉ…
ግብ አዳኝ… መሀመድ ሳላህ… ከግብፅ
አልፎ… በመላው ዓለም… ዝናው
ናኝቷል…፤ ግብፃዊያን… ለግብፃዊው ሜሲ…
ያላቸውን አድናቆትና… ስሜትን… እንዴት
ታዘብከው…?

ሽመልስ፡- …ግብፃዊያን… ለሳላህ
ጥሩ ስሜት አላቸው…፤ የጀግናቸው…
የንጉሳቸው… ያህል ነው የሚያዩት…፤…
በግብፅ… በጣም የሚወደድና… የሚመለክ…
ተጨዋች ነው…፡፡
ሀትሪክ፡-…በሀገር ውስጥም…
በውጪም… በብዙ አሰልጣኞች… የመሰልጠን
እድል አግኝተሃል… የተለየ ቦታ የምትሰጠው
አሰልጣኝ ማነው…? …ብልህ… መልስህ …
ምንድነው..?
ሽመልስ፡ …የየራሳቸውን አሻራ…
በውስጤ ያሳረፉ ብዙ አሰልጣኞች አሉ…፤…
ከሀገር ውሰጥ ስጀምር… በብ/ቡድን ደረጃ…
አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው…፣… አሰልጣኝ
ዮሐንስ ሳህሌና… አሁን ላለው የአሰልጣኞች
ቡድን… የተለየ ቦታ አለኝ…፡፡ …የውጪ
ሀገር ዜግነት ካላቸውና ካሰለጠኑኝ…
አሰልጣኞች ደግሞ… ጊዮርጊስ እያለሁ…
ክሩገር… በብ/ቡድን… ለኤፌም ኦኑራ…
የተለየ ቦታ አለኝ…፡፡
ሀትሪክ፡- …ከማን ጋር ስትጫወት…
ወይም… ማን አጠገብህ ሲኖር… ጨዋታ
ይቀልሃል…?
ሽመልስ፡- …ብዙ አሉ… ከአዲስ ሕንፃ
ጋር…፣ ከመስዑድ መሀመድ…፣ ከምንያህል
ተሾመና ከራሱ ከሙሉጌታ ምህረት ጋር…
አብሮ መጫወት ጨዋታውን ያቀላል…፤ …
አብሬ ስጫወትም ይመቸኛል…፡፡
ሀትሪክ፡-….አብረኸው ባለመጫወትህ
የምትቆጨውና… አብሬው ብጫወት ኖሮ…
ብለህ… የምትመኛቸው ማነው…?
ሽመልስ፡- …ሙሉጌታ ምህረትን…
እያደነኩ ስላደኩ… ከእሱ ጋር… አብሬ
መጫወትን እፈልግ ነበር፤.. አብሬው
ባለመጫወቴ ብቆጭም… አሁን… በብ/
ቡድን ደረጃ… አብረን የምንሰራበት… እድል
ስለተፈጠረ …ቁጭቴ ቀንሷል…።
ሀትሪክ፡- …ከሐዋሳ የተነሣው…
የሽመልስ በቀለ በቀለ ህይወት…
በፕሮፌሽናልነት ታጅቦ ግብፅ ደርሷል….፤
ሽመልስ… ከትናንት… ዛሬ …ተለውጧል…
?
ሽመልስ፡- …መጀመሪያ ከነበረው…
ሳስበው… አሁን ብዙ የአዕምሮ ለውጦች
አሉኝ…፤… እግር ኳስን በተመለከተ…
ያለኝ ሜንታሊቲ (አስተሳሰብ)… በጣም
ተለውጧል ማለት እችላለሁ…፤ አሁን
ያለው አስተሳሰቤ… በፕሮፌሽናልነት ተቃኝቶ
ሰፍቷል…፡፡ …በአጭሩ… ልልህ የምችለው…
በፊት የነበረኝን ሜንታሊቲ (አስተሳሰብ) …
አልረሳሁትም… ይበልጥ አሳደኩት እንጂ…፡፡
ሀትሪክ፡- …በኑሮስ ደረጃ… ሽመልስ
አምልጧል… የናጠጠ ሀብታም ሆኗል…?
ሽመልስ፡- …በጣም ሳቅ… እግዚአብሔር
ይመስገን… ያጣሁት ነገር የለም…፡፡
ሀትሪክ፡- …ከሀገር ውስጥ ይሁን
ከውጪ… እየተከታተለ አላንቀሳቅስ እያለ…
የሚያስቸግርህ ተጨዋች አለ… ?
ሽመልስ፡- …በዚህ ደረጃ… አስቸገረኝ
ብዬ… የምጠራው ተጨዋች የለም…፡፡
ሀትሪክ፡- …ከአንተ በፊት… የአማካይ
ክፍል ንጉሶች በሚል… አሸናፊ ግርማና
ሙሉአለም ረጋሳን… ያሞካሻሉ… በእዚህ
ዙሪያ… ምን ትላለህ…?
ሽመልስ፡- … እውነት ነው… ሁለቱም…
ምርጥ አማካዮች ናቸው…፤ ከአሸናፊ ግርማ
ጋር የመጫወት እድል አግኝቼ በቅርበት
አጨዋወቱን አይቼዋለሁ…፤ …ከሙሉአለም
ጋር… የመጫወት እድል ባላገኝም… እውነት
ነው ሀለቱም …ምርጥ አማካዮች ናቸው…፡፡
ሀትሪክ፡- …ከእነሱ በኃላ… የተዋጣላቸው
አማካዮች… አልተፈጠሩም የሚሉ አሉ…
ይሄስ… ይስማማሃል…?
ሽመልስ፡- … እነሱ በጣም ጥሩና
ምርጥ አማካዮች ናቸው… ይሄንን መካድ
አይቻልም…፤… ከእነሱ በኋላ ግን…
የአማካይ ተጫዋች በሀገሪቱ አልተፈጠረም…
ብሎ መፍረድም መልካም አይመስለኝም…፤
…ምክንያቱም… ከእነሱ በኋላም ብዙ
ተፈጥረዋል ብዬ ስለማምን…፡፡
ሀትሪክ፡- …ባህር ዳር ላይ…
ከኬንያ ጋር በነበረው ጨወታ…
የሚድፈልድ ጦርነት (Midfield battle)…
በአንተ፣ በጋቶች፣ በሙሉአለም መስፍንና
በኬንያው ዋኒያማ መካከል ነበር…፤…
ይሄንን ጨወታ… እናንተ በበላይነት…
መወጣታችሁን… ብዙዎች ይገልፃሉ…
አንተስ… በዚህ ላይ… ምን ትላለህ…?

ሽመልስ፡- … በእርግጥ ሜዳ ላይ
ስትሆን… ትኩረትህ ውጤት ላይ
ነው…፤… ይሄንን ውጪ ያሉ… ልብ ሊሉ
ይችላሉ…፤… አኔም ግን… መሀል ላይ…
ብልጫ እንደወሰድንባቸው (Dominate)…
እንዳደረግናቸው… ይሰማኛል…፤ …
በጨዋታ እንቅስቃሴ በልጠናቸዋል…፤…
ኳሱን… ከእነሱ በላይ… አንቀሳቅሰነዋል…
ብዬ አስባለሁ…፡፡
ሀትሪክ፡- …ቪክቶር ዋኒያማ… በአለማ
ችን ትልቁ ሊግና ትልቅ ክለብ ለሆነው
ቶተንሃም የሚጫወት ተጫዋች ነው፤በዚህ
ደረጃ ያለው ተጫዋች በሜዳ ላይ የጎላ ልዩ
ነትን ሲፈጥር ልብ ብለህ አስተውልሃል… ?
ሽመልስ፡- እንዳልከው ትልቅ ሊግ
ውስጥና ትልቅ ክለብ ውስጥ የሚጫወት
ተጫዋች በመሆኑ ክብር አለኝ፤ የሌሎችን
ተጫዋቾች አላውቅም፤ እንኳን እሱ ማንም
ተጫዋች ቢመጣ ከዚህ ክለብ መጣ እንዲህ
ተጫወተ የሚለው ብዙም አያሳስበኝም፡፡
ከዚህኛው ይልቅ ሜዳ ውስጥ በሚያሳያቸው
ነገሮች ነው ዋጋ የምሰጠው፤ ከኬንያዊው
ዋኒያማ ይልቅ ሙሉአለምና ጋቶች ለእኔ
በጣም ጥሩ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ግን በእግር
ኳስ ያው ችሎታ ብቻ ሣይሆን እድልም
ያስፈልጋል፤እሱ እዛ ገብቶ እንዲጫወት
እድል ጠቆሞታል፤ የእኛም ልጆች እድል
ቢያጋጥማቸው የተሻለ መጫወት እንደሚችሉ
በነበራቸው ግልፅ ብልጫ አሳይተዋል፡፡
ሀትሪክ፡- በባህርዳሩ ጨዋታ ሁለት
ያለቀላቸው ጎሎችን መሳትህ በውስጥህ ምን
አይነት የቀጭት ስሜት ፈጠረ?
ሽመልስ፡- ጎልን ታርጌት አድርገህ በእግር
ኳስ ውሳኔ ስትወስን ወይ ታገባለህ ወይ
ትስታለህ…፤ ካለፈ በኋላ በጣም የምትቆጨው
ሰው ከሚነግርህ በላይ ቪዲዮዎችን መላልሰህ
ስታይ ነው፤ እንዲህ ቢሆን እንዲህ ባላረገው
የምትለው። መጀመሪያ ኃላፊነቱን ወስጄ ወስኜ
ስሞክር ጎል ይሆናል ከሚል የእርግጠኝነት
ስሜት ነው፤ ኳስ ነው ያጋጥማል፡፡
የሆነው ነገርም ያስቆጫል፤ በተለይ የግቡ
ቋሚ አግዳሚ ገጭቶ የወጣው ኳስ በጣም
የሚያስቆጭ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …ባህር ዳር ላይ… የነበረው
የጋምቢያዊው ዳኘነትስ… ተስማምቶሃል…?
ሽመልስ፡- …ካለፈ በኋላ ምክንያት
ለመደረደር ሳይሆን… የዳኝነት ተፅዕኖ
ነበረብን… በእኔ የግል እይታ… ዳኛው…
ወደ ሶስት የሚሆኑ የፍፁም ቅጣት ምቶችን
ከልክሎናል…፤ …ይሄ ዳኛ… ከዚህ
በፊትም እንደምታውቀው… ከናይጄሪያ ጋር
ስንጫወት… በዳኝነቱ አልተደሰትንበትም…፤
የገባ ኳስ አላፀደቀልንም…፡፡ … ስትጫወት…
ኳስ በውስጡ… ብዙ ነገሮች አሉበት…፡፡
ሀትሪክ፡- …በባህርዳር ስታዲየም…
የነበረው ደጋፊ… በተጋጣሚ ቡድን
አሰልጣኝ፣ በሚዲያዎች ሳይቀር ከፍተኛ
አድናቆት ተችሮታል…፤ አንተስ ይሄንን
ሀገሩን እግር ኳሱን የሚወደውን ደጋፊ
እንዴት ነው የምትገልፀው… ?
ሽመልስ፡- …ደጋፊውን…? …ይሄን
ደጋፊ… በትክክል የሚገልፅ ቃላት የለኝም…፤
ደጋፊው ከቃላት በላይ ነው…፡፡ …እውነት
ለመናገር… ሀገራችን የባህር ዳር ህዝብ ለኳስ
የተለየ ፍቅር እንዳላቸው በግልፅ አሳይተዋል፤
የተለዩ ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ደጋፊዎቹ
ከጎናችን በመሆናቸው በጣም ከፍተኛ ደስታ
ተሰምቶኛል፡፡
ሀትሪክ፡-በዚህ ደረጃ የገለፅካቸውና
ስታዲየሙን ከአፍ እስከገደፉ የሞሉት
ደጋፊዎች ሶስት ነጥብ አግኝተው ጨፍረው
ባለመመለሳቸው ምን ስሜት ተፈጠረብህ… ?
ሽመልስ፡- በጣም ያንገበግበኝም ይሄ
ነው…፤ ለዚህ ደጋፊ የሚገባው ይሄ
አልነበረም፡፡ አሸንፈን ሶስት ነጥብ አግኝተን
ቦርቀው ተደስተው ቢወጡ ከእነርሱ በላይ
የምንደሰተው እኛ ነበርን፤ ግን አልሆነም፤
በዚህ ሁላችንም በጣም አዝነናል፡፡ ውጤቱ
ምንም ይሁን ምን ደጋፊው ግን በአደጋገፉና
በጨዋነቱ አሸንፎ ወጥቷል፤ እስከዛሬ ሁለት
ጊዜ ባህርዳር ላይ ተጫውቻለሁ ሽንፈት
አላጋጠመኝም፤ ደጋፊው ፍፁም ልዩ
ነው፤ እነሱም መላው የኢትዮጵያ ህዝብም
እንዲደሰት ነበር ፍላጎታችን፤ ደጋፊው
ላሳየው ጨዋነት የተሞላበት ድጋፍ ክብር
ይገባቸዋል፡፡
ሀትሪክ፡- …ቆይታዬን ከመቋጨቴ በፊት
እስቲ … ስለግል ህይወትህ እናውራ…
የፍቅር ሰው ነህ…?
ሽመልስ፡-..እንደመገረም ብሎ…
ማለት…?
ሀትሪክ፡- …አፍቅረህ … ታውቃለህ…
ወይ…ለማለት…ነው…?
ሽመልስ፡- …አሁንም…ኮስተር ብሎ…
አፍቅረህ ታውቃለህ ወይ…ነው…ያልከው…?
ሀትሪክ፡- እንዴ…ሽሜ ምነው በሰላም
ነው!…እሺ… የፍቅር ጓደኛስ አለህ… ?
ሽመልስ፡ …ታዲያ እንደዚህ አትልም…
(ሳቅ)… አዎን…አለኝ…! የነገ… የትዳር
አጋሬ የምትሆን …የፍቅር ጓደኛ አለችኝ፡፡
ሀትሪክ፡- …በአራዳዎች ቋንቋ…
የትና…?… እንዴት…? ጠበስካት…?
ሽመልስ፡-…(ሣቅ)…የሓዋሳ ልጅ ናት…፤
የተዋወቅነው በስልክ ነው…በቃ…ይሄው…
ነው…፡፡

ሀትሪክ፡- …በስልክ ስትል…? ስልክ
በስጦታ መልክ ሰጠሃት…ማለት…ነው…?
ሽመልስ፡- … አሁንም … ሳቅ… ኧረ
አይደለም… በስልክ ተደዋውለን… በአድናቆት
ተዋውቀን ነው… ጓደኛ የሆነው…።
ሀትሪክ፡- …. ይሄ የፍቅር ግንኙነት…
መቼ አድጎ… ወደ ትዳር አጋርነት ይቀየ
ራል…? …በአንድ ጣሪያ ስር… የመኖር…
ጎጆ የመቀለስ… እድቅስ የላችሁም…?
ሽመልስ፡- …ሁሉንም ነገር የሚወስነው…
እግዚአብሔር ነው…፤ …እንደ እኛ ሃሳብ…
እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ …በሁለት
አመት ውስጥ…ይሄ እውን… የሚሆን…
ይመስለኛል…፤ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ…
ጋብቻ መስርተን… አብረን እንኖራለን… ብዬ
አስባለው….፡፡
ሀትሪክ፡- …ለነበረን ጊዜ ለስጠኸኝ ክብር
ከልቤ እያመሰገንኩ…፤ …እግዚአብሔር
የልብህን ያሳካልህ… የመጨረሻው መልካም
ምኞቴ ነው…?
ሽመልስ፡- … ወዲያው… ብድግ እያለ…
እኔም ከልብ አመሰግናሃለሁ…ቻው…፡፡
አስተያየት ይስጡ