በሀዋሳ ከተማ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንት ሶስት ተጫዋቾችን የቀነሰ ሲሆን በዛሬው እለት አራት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ቀንሷል።

የነገሌ አርሲው አማካይ ዳዊት ተፈራ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለቆ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በጣምራ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው አጥቂው ናትናኤል ዳንኤል ፤ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ለቆ ሀድያ ሆሳዕናን የተቀላቀው የግራ መስመር አጥቂው እዮብ ገ/ማርያም እና ኢትዮ ኤሌክትሪክን ለቆ ቅዱስ ጊዮርጊስን የተቀላቀለው የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ የማነ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ ሆነዋል
አስተያየት ይስጡ