አዳማ ከተማ የፊታችን ሰኞ ልምምድ ይጀምራሉ።

በቀጣዩ የ2019 የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከሚካፈሉ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው አዳማ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙ የሚታወስ ሲሆን በርካታ ተጫዋቾች በክለቡ ውል ቢኖራቸውም የአራት ተጫዋቾችን ዝውውር በማጠናቀቅ ወደ ዝግጅት ለመግባት መቃረቡን ያገኘውት መረጃ ይጠቁማል።
የፊፋችን ሰኞ ነሐሴ 18/2018 ክለቡ በመቀመጫ ከተማው የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚጀምር ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ