ሊጉ የሚደረግባቸው ስታዲየሞች ታወቁ።

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 እንደሚጀመር ይታወሳል። አስራ ስምንት ክለቦች በሚሳፉበት የሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን በሰባት ስታዲየሞች እንዲደረግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በሦስት ዙር በየስታዲሞቹ ተዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ ውሳኔ ማሳለፉን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።
በዚህም መሠረት አዲስ አበባ ስታዲየም ፣ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ፣ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ባሉበት ሲቀጥሉ የባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየምም ከአመታት በኋላ የሊጉን ውድድር የሚያስተናግድ ሲሆን የሀላባ ስታዲየም ፣ የሆሳዕናው አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም ፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ያስተናግዳሉ።
ስለሆነም ፕሪምየር ሊግ በስድስት ቋት ተከፍሎ በአንድ ሜዳ ላይ በደርሶ መልስ መልኩ የሚደረግ ሲሆን ይህም በአንድ ከተማ ረጅም የውድድር ጊዜን ከማሳለፉ ለክለቦች እፎይታን የሰጠ ጉዳይ መሆኑን ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ