በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ዘለግ ላሉ አመታት በአሰልጣኝነት የሚታወቀው አምጣቸው ሐይሌ የአሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌው ኢትዮጵያ ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።

ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን መነሻውን ካደረገ በኋላ በዋናው ቡድን ለአስር አመታት ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ያገለገለው አሰልጣኝ አምጣቸው በከፍተኛ ሊጉ ካፋ ቡና ዋና አሰልጣኝ በሲዳማ ቡና እና እንዲሁም ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ወላይታ ድቻን በረዳት እና በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ከመራ በኋላ የኤ ላይሰንስ ባለቤቱ እና የካበተ ልምድ ያለው አምጣቸው ሐይሌ የቡናማዎቹ ረዳት ሆኖ በይፋ መሾሙን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ