ከፕሪምየር ሊጉ ከአመታት ቆይታ በኋላ የወረደው እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2019 የውድድር ዘመን ላይ እንደሚካፈል የሚጠበቀው ድሬዳዋ ከተማ ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ሲስማማ የሁለት ነባሮች ውል ደግሞ አደሰ።

ወደ ቀደመ ክለቡ በድጋሚ የተመለሰው ተከላካዩ ሚኪያስ ካሳሁን ፣ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና በቅዱስ ጊዮርጊስ መለያ ጥሩ የውድድር ዘመን ማሳለፍ የቻለው የተከላካይ አማካዩ ብርሀኑ አሻም ፣ በሸገር ከተማ እና በነቀምት ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው እስጢፋኖስ ቶማስ ፣ ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በዱራሜ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያሳለፈው አማካዩ በዛብህ ካቲሶ ፣ የቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ የተጠናቀቀውን አመት በሸገር ከተማ ያሳለፈው ግብ ጠባቂው ምንተስኖት የግሌ እና የቀድሞው የድሬዳዋ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ላለፉት ስድስት ወራት በአርባምንጭ ከተማ የነበረው ተከላካዩ አማረ በቀለ፣ በመቻል እና ንግድ ባንክ የምናውቀው አማካዩ ፊሊሞን ገብረፃዲቅ እና በምድረገነት ሽረ ያለፉት አመታት የተጫወተው አጥቂው ናትናኤል ተክለ አዳዲሶቹ የድሬዳዋ ከተማ ፈራሚ ሆነዋል።
ክለቡ የአጥቂው ዘርአይ ገብረስላሴ እና የአማካዩን ሔኖክ ሀሰንን ውል ደግሞ አራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ