አለምብርሀን ይግዛው እና አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ጉዳይ ውሳኔ አገኘ።

በያዝነው የክረምቱ የዝውውር መስኮት መነጋገሪያ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል በመቻል ውላቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ለኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ስምምነት ውል ለመቻል ደግሞ ውል በማደሳቸው ለሁለት ክለቦች የፈረሙ በሚል የመስመር ተከላካዩ አለምብርሀን ይግዛው እና አማካዩ አብዱልከሪም ወርቁ ጉዳይ ሲያወዛግብ መቆየቱ ይታወሳል።
ይህንንም ጉዳይ ለሳምንታት ሲመለከት የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በመጨረሻም ተጫዋቾቹ በህጋዊነት ደረጃ ለመቻል በፌዴሬሽኑ በመፈረማቸው ክለቡን እንዲያገለግሉ ሲወሰን ነገር ግን ተጫዋቾቹ ለሁለቱም ክለብ መፈረማቸው ስስተት በመሆኑ ከመስከረም 30/2019 ጀምሮ በሚቆጠር ወር ለአራት ወራት እንዳይጫወቱ ሲታገዱ የሁለት መቶ ሺህ የገንዘብ ቅጣትም እያንዳንዳቸው እንዲቀጡ ተወስኗል።
አስተያየት ይስጡ