በአቤኔዘር አበበ
በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሸገር ሲቲ ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወሳኝ ሦስት ነጥብ አሳክቷል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሸገር ሲቲ በዳዊት ካሳው አማካኝነት አደገኛ ሙከራ ቢያደርግም፣ የኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ ኳሷን በመመለስ ቡድኑን ከግብ አደጋ ታድጓል። አጋማሹም ያለ ግብ ተጠናቋል።

ከዕረፍት መልስ ኢትዮጵያ ቡና በማጥቃት የተሻለ እንቅስቃሴ ቢያሳይም፣ ወሳኙን ግብ ማስቆጠር አልቻለም። በ85ኛው ደቂቃ ካሌብ በየነ ከቅጣት ምት ያስቆጠራት ግብ የጨዋታውን ሚዛን በመቀየር ለሸገር ሲቲ ወሳኝ ድል አስገኝታለች። ይህች በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የተገኘች ግብ ለቡድኑ ሙሉ ሦስት ነጥብ ከማስገኘቷም በላይ፣ ከሜዳው ውጪ የተገኘ ወሳኝ ድል እንዲመዘግብ አስችላለች።
የመጨረሻ ውጤት፦ ኢትዮጵያ ቡና 0–1 ሸገር ሲቲ
አስተያየት ይስጡ