መነሻ ገጽ መቻል መቻል እና ንግድ ባንክ የሊጉን ጉዞ በድል ጀመሩ
መቻልኢትዮጵያ ንግድ ባንክዜናዎች

መቻል እና ንግድ ባንክ የሊጉን ጉዞ በድል ጀመሩ

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረጉ የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች መቻል ሀዋሳ ከተማን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ሲዳማ ቡናን በደጋፊዎቻቸው ፊት ረተዋል።

በሀዋሳ ከተማና መቻል መካከል በተደረገው ጨዋታ ደካማ እንቅስቃሴ በታየበት የመጀመሪያ አጋማሽ ሀዋሳ ከተማ በጌታነህ ከበደ አማካኝነት ከቆመ ኳስ ዒላማውን የጠበቀ አንድ ሙከራ ሲያደርግ፣ መቻል ዒላማውን የጠበቀ ሙከራ ሳያደርግ ወደ ዕረፍት አምርቷል።

በሁለተኛው አጋማሽ መቻል በመሐል ሜዳ ቁጥጥር ላይ የበለጠ ብልጫ በማሳየት ጨዋታውን ተቆጣጥሯል። የሁለቱም አሰልጣኞች ቅያሪዎች በጨዋታው ላይ ተጽዕኖ ቢፈጥሩም፣ በ84ኛው ደቂቃ ቢንያም ተክሉ ያስቆጠራት ግብ ለመቻል የ1 ለ 0 ድልን አስገኝታለች።

 

በሌላ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተገናኝቷል። በመጀመሪያው አጋማሽ በተደጋጋሚ ፋውሎች በታዩበት ጨዋታ፣ የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች ያሬድ ባዬ እና መስፍን ታፈሰ በጉዳት በ13ኛው ደቂቃ ተቀይረው ከሜዳ ወጥተዋል።

በ43ኛው ደቂቃ ሄኖክ ኤርሚያስ የሲዳማ ቡናን የመከላከያ ክፍል አለመናበብ ተጠቅሞ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድል ግብ አስቆጥሯል። በሁለተኛው አጋማሽ ሲዳማ ቡና ጫና ፈጥሮ በተደጋጋሚ ወደ ግብ ቢደርስም፣ ሙከራዎቹን ወደ ግብነት መቀየር ተስኖት በአንድ ግብ ልዩነት ተሸንፏል።

የጨዋታዎቹ ውጤት

ሀዋሳ ከተማ 0–1 መቻል

ሲዳማ ቡና 0–1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...