በአቤኔዘር አበበ
በሀላባ አዲሱ ስታዲየም የተገናኙት ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ 0ለ0 ተለያይተዋል።
በጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ግልጽ የግብ ዕድሎችን ሳይፈጥሩ ወደ ዕረፍት አምርተዋል።

ከዕረፍት መልስ ቡድኖቹ ቅያሪዎችን በማድረግ የጨዋታውን ውጤት ለመቀየር ቢጥሩም ግብ ማስቆጠር ላይ ግን ሳይሳካላቸው ጨዋታው ያለ ግብ ተጠናቋል።
በዚህም የጦና ንቦቹና አፄዎቹ አንድ አንድ ነጥብ ተጋርተዋል።
አስተያየት ይስጡ