በአቤኔዘር አበበ
በመጀመሪያ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርሲ ነገሌ ጋር 1-1 በሆነ ውጤት ፈፅመዋል።

በመጀመሪያዎቹ 10 ደቂቃዎች ነገሌዎች የተሻለ እንቅስቃሴን ለማሳየት ጥረትን ቢያሳዩም ቅዱስ ጊዮርጊሶች በቀሩት ደቂቃዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫን በመያዝ ጫና ፈጥረው በድግግሞሽ ሲጫወቱ አስተውለናል።

ከዕረፍት መልስ 51ኛው ደቂቃ ከቆመ ኳስ ያሬድ የማነ የደረሰውን አጋጣሚ ወደ ውስጥ ሲያሻማ አዲሱ ፈራሚ ናትናኤል ዳንኤል በግንባር ገጭቶ በማስቆጠር ፈረሰኞቹን መሪ ቢያደርግም ነገሌ አርሲዎች 62ኛው ደቂቃ የጋናዊው አጥቂ ኮሊንስ ኮፊ የግል ጥረት ታክሎበት ለዳዊት ተፈራ አሾልኮ የሰጠውን ኳስ በጥሩ አጨራረስ አምበሉ ከመረብ አዋህዶ ጨዋታው እጅግ ድንቅ ፉክክር ተስተውሎበት 1ለ1 ተጠናቋል።

አስተያየት ይስጡ