ሀያ አምስት አመታቶችን በዳኝነት ያገለገሉት ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም በይፋ ማቆማቸውን አሳውቀዋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ የዳኝነት ታሪክ ውስጥ ከፊት ከሚጠሩ ዳኞች መካከል መሆን የቻሉት በኢንተርናሽናል ዳኝነት በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ሀያ አምስት አመታቶችን ያገለገሉት የቀድሞው ኢንተርናሽናል ዳኛ ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው ከዳኝነት አለም በይፋ ማቆማቸውን አሳውቀዋል።
ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ጋር ከረር ባለ ፀብ ውስጥ ይገኙ የነበሩት እና በዳኝነት እንዳይሰሩ መደረጋቸውን ሲቃወሙ የሰነበቱት የባህርዳር ዩኒቨርስቲ መምህሩ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዳኛው በቀጣይ አዳዲስ ዳኞችን ማብቃት ላይ የነበራቸውን ልምድ ተጠቅመው መስራት እንደሚፈልጉ መናገርም ችለዋል።
አስተያየት ይስጡ