በኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ወልዋሎ ዓ/ት ዩኒቨርስቲ በመለያ ምት መቻልን በመርታት ወደ ግማሽ ፍፃሜው ያለፈ ሁለተኛው ክለብ ሆኗል።

ትላንት መቐለን ወደ ግማሽ ፍፃሜው በማሳለፍ ጅምሩን ያደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ መርሀግብር በሁለተኛ ቀኑ ዛሬም ቀጥሎ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲን ከመቻል ያገናኘ ነበር። መቻሎች በብዙ ረገድ በሁለቱም አጋማሾች በተሻለ ለመጫወት ጥረት ባደረጉበት ጨዋታ የሚያገኟቸውን ዕድሎች መጠቀም ባለመቻላቸው በመጨረሻም ለሽንፈት ተዳርገዋል።

በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ አምበሉ እና አማካዩን ፍሬው ሠለሞንን በሁለት ቢጫ ካርድ ለማጣት የተገደዱት ወልዋሎዎች ጨዋታው ያለ ጎል መጠናቀቁን ተከትሎ በተሰጠው የመለያ ምት በዩጋንዳዊው የግብ ዘብ ሙታክብዋ ጆኤል አስደናቂ ብቃት ታግዘው 5ለ4 በሆነ ውጤት አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል።

ነገ ጨዋታው ሲቀጥል የከፍተኛ ሊጉ ቤንች ማጂ ቡና ከኢትዮጵያ መድን ቅዳሜ ደግሞ ነገሌ አርሲን ከ ሲዳማ ቡና ያገናኛል።
አስተያየት ይስጡ