መነሻ ገጽ Uncategorized በፌዴሬሽኑና በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ መካከል የሥራ ውል ስምምነት ተፈረመ
Uncategorized

በፌዴሬሽኑና በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ መካከል የሥራ ውል ስምምነት ተፈረመ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ከሥራ ማሰናበቱን ተከትሎ ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም በፌዴሬሽኑና በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ መካከል የሥራ ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡567890876545566778987654
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በገብረመድን ኃይሌ መካከል የተፈረመው የሥራ ውል ከግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2009 ዓ.ም ለአምስት ወራት የሚቆይ ነው፡፡
በተጠቀሱት ወራት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዳሬሽን ለአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በየወሩ ያልተጣራ ብር 80,000.00/ሰማኒያ ሺህ ብር/ ይከፍላል፡፡ የቴሌፎን ፣ የኃላፊነትና የነዳጅ ጥቅማ ጥቅሞችንም ይጠብቃል፡፡
አሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ለሁለት ቀሪ የማጣሪያ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
በአሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌና በፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች መካከል ውይይት በተደረገበት ወቅት ለአሰልጣኝ ገብረመድን እንደተገለፀው ለብሔራዊ ቡድን በመጫወት ያገኘው ትልቅ ክብር ለእዚህ ከባድ ሃገራዊ ኃላፊነት ስምምነቱንና ፈቃደኝነቱን በመግለፅ ብሔራዊ ግዴታውን ለመወጣት ያስገደደው ሆኗል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከሲሼልስ የማጣሪያ ጨዋታ ጀምሮ ያስመዘገበውን ዝቅተኛ ውጤት ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ፈጣን ርምጃ ለመውሰደ ክፍተት እንደተፈጠረ በመቁጠር የተቀበለው ሲሆን በቀጣይነት ውስጣዊ የአሠራር ሥርዓት ማስተካከያ የማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በሂሳባዊ ስሌት የቡድናችን ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ተስፋው ሙለ በሙለ ያልተሟጠጠ በመሆኑም ፌዴሬሽኑ በእግር ኳስ ቤተሰቦች ዘንድ ከፍተኛ ከበሬታ የሚሰጠውን ገብረመድን ኃይሌን በጊዜያዊ አሠልጣኝነት እንዲሾም አዴርጓል፡፡ አሠልጣኝ ገብረመድን የተረከበውን ከባድ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣና ቡድናችን የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ የእግር ኳስ ቤተሰቦች የተለመደ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉም ፌዴሬሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...