ኩሪ አጥቁ በትናንትናው ዕለት ከባለቤቷ ሄኖክ አዳነ ጋር የጋብቻ ስነ-ስርዓቷን በደማቅ ሁኔታ ለመፈፀም ችላለች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ እና በክለብ ደረጃ ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና እና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከላካይ ስፍራው ላይ ኳስን በእውቀት ከሚጫወቱ ጥቂት ተጨዋቾች መካከል አንዷ የነበረችው እና በአሁን ሰዓት ደግሞ የመከላከያ ክለብን እያገለገለች ያለችው ኩሪ አጥቁ በትናንትናው ዕለት ከባለቤቷ ሄኖክ አዳነ ጋር በትውልድ ክልሏ ደብረብርሃን ከተማ የጋብቻ ስነ-ስርዓቷን በደማቅ ሁኔታ ለመፈፀም ችላለች። ለሴቶች እግር ኳስ ዕድገት ጥሩ አስተዋጽኦ ካደረጉት ተጨዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ኩሪ ትናንት ጋብቻዋን ስትፈፅም ሚዜዎቿ የነበሩት በጥሩ የኳስ ብቃታቸው ይታወቁ የነበሩት እና በተለያዮ ቡድኖች ውስጥ ተጫውተው ያሳለፉት የቅዱስ ጊዮርጊሷ ሃና ቱርጋ እና የአዳማ ከተማዋ እታገኝ ሰይፉ ናቸው። ለኩሪ አጥቁ እና ባለቤቷ ሄኖክ መልካም ጋብቻ ብለናል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team