መነሻ ገጽ Uncategorized ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?
Uncategorized

ለዋልያዎቹ መጫወትን የሚመኘው የሴሪ ኣው ክለብ ተጫዋች ማነው ?

አጋራ
አጋራ

የጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ቶሪኖ ንብረት ስለሆነው አስደናቂው የአጥቂ አማካይ ተጫዋች እንንገራችሁ።

እናቱ ጣሊያናዊ ስትሆን አባቱ ደግሞ በስምንት አመቱ ለጎዲፈቻ ወደ ጣሊያን ተወስዶ በሚላን ከተማ ካደገ ኢትዮጵያዊ የተገኘ ነው። ከእነኚህ ከሁለቱ ጥንዶች የተገኘው አማካዩ አሮን ሲያማግሊ ቼላ በጣሊያኗ ቱሪን ከተማ የተወለደ ሲሆን አሁን ዕድሜው 21 አመቱ ላይ ደርሷል። በጣሊያን እያበበ የመጣው አስደናቂው የአጥቂ አማካዩ ወጣት ተጫዋች በጣሊያን ሴሪኣ ከሚሳተፈው ቶሪኖ ወጣት አካዳሚ በመነሳት በመቀጠልም በቶሪኖ ከ17 ፣ ከ18 እና ከ19 አመት በታች ቡድኖች ውስጥ ያሳየውን ተከታይ ብቃት ተከትሎ ልክ የዛሬ ሦስት አመት አካባቢ ወደ ዋናው የጣሊያን ሴሪ ኣ ወደ ሚሳተፈው ቶሪኖ በማደግም አሳዳጊ ክለቡን በሚገባ ሲያገለግልም ቆይቷል።

ከቶሪኖ ጋር አሁንም ኮንትራት ያለው እና በውሰት ውል በጣሊያን ሴሪ C ቴራና ክለብ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በጣሊያን ሴሪ B በሚካፈለው ጁቬ ስታቪያ የሚገኘው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ለጣሊያን ከ15 ፣ ከ16 ፣ ከ17 ፣ ከ19 እና ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ በመጫወት አውሮፓዊቷን ሀገር በአለም እና በአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች በአግባቡ መወከል የቻለ ሲሆን በቅርቡም ጣሊያን ከ እንግሊዝ ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር ከሚኖረው የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ የአባቴን ሀገር ኢትዮጵያን ማገልገል ከፍተኛ ፍላጎት አለኝ ሲል ይናገራል።

ከሦስት ወራት በኋላ የውሰት ውሉን አጠናቆ ወደ ወደ ሴሪ ኣው ቶሪኖ እንደሚመለስ የሚጠበቀው ይህ አማካይ ህልሙ ተሳክቶ የዋልያዎቹን መለያ ይለብስ ይሆን የሚለው ጉዳይ እጅጉን ያጓጓል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
Uncategorized

ቅዱስ ጊዮርጊስ የመቶ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገለት

ዛሬ አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፓርት ማህበር ከገጠመው የመፍረስ አደጋ ለመታደግ የተለያዩ አካላትን...

Uncategorized

ቡናማዎቹ ተጫዋች ለማስፈረም ተስማሙ !

  በዛሬው ዕለት ግብ ጠባቂ በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ኢትዮጵያ ቡናማዎች ዘካሪያስ...

The BiG InterviewUncategorizedኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

“የኢትዮጵያ ቡናን ማልያ ለብሼ እንድጫወት ትልቁ ምክንያት የሆነኝ በቃላት የማይገለፀው ደጋፊው ነው”ወንድሜነህ ደረጀ (ኢት.ቡና)

ክፍል ሁለት  በይስሐቅ በላይ ወንድሜነህ፡- …እኔ እንደዛ ነው የሚሰማኝ…በነገሮች ሃሣቡን የማይቀይር የራስ...