ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ በስፔን የሴጎንዳ ዲቪዚዮን በመጫወት ላይ የሚገኘው የመሐል ተከላካይ።
ከኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦች የተገኘው እና በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ የተወለደው የመሐል ተከላካዩ ፍሮምሳ ማቲዮ ካታላ ይባላል። 24 አመቱ ላይ የሚገኘው እና ዕድሜው አስርን ሳይደርስ ወደ ስፔን ያመራው ይህ ተከላካዩ እግር ኳስን የጀመረው በዛው በስፔን ኬልሚ በተባለ ከ19 አመት በታች ቡድን ሲሆን በመቀጠልም ሁካም ሙርሺያ ኤፍ ሲ ካርቴገና ፣ ፑልፒሊኖ እና አንቶኒያቶ ተብለው ለሚጠሩ በስፔን የታችኛው ዲቪዚዮን ለሚገኙ ክለቦች በመጫወት አሳልፏል።
በአሁኑ ሰዓት በስፔን ሴጉንዳ ዲቪዚዮን ሎርካ ዲፓርቲቮ እየተጫወተ የሚገኘው አንድ ሜትር ከሰማንያ ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ይህ ተጫዋች ተወልዶ ላደገባት ኢትዮጵያ መጫወትን እጅግ አጥብቆ ይመኛል።

አስተያየት ይስጡ