ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀድሞው አጋሩ ጋር በድጋሚ ለመጣመር ውይይት አድርጓል።
አንጋፋውን የቅዱስ ጊዮርጊስን ክለብ ከገጠመው የፋይናንስ እና የአስተዳደር ችግር ለመቅረፍ ይረዳ ዘንድ በቅርቡ የተመረጠው ጊዜያዊ የሽግግር ኮሚቴ የቀድሞው የክለቡ ታሪካዊ ስፖንሰር አድራጊ የሆነውን ቢ ጂ አይ ኢትዮጵያን በድጋሚ ለመመለስ ጥረቶች ተደርገው ተገባደዋል።

ከተቋሙ ጋር ከዚህ በፊት ያለውን የአጋርነት ውል ለማስቀጠል በትናንትናው እለት ከቢ ጂ አይ ኢትዮጵያ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉ የተነገረ ሲሆን በመጨረሻም አጋርነታቸውን ለማስቀጠል ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት የቢጂአይ ሀላፊዎች የገለፁ ሲሆን በቀጣይም ስምምነቶችን ለመፈፀም ከስምምነት መደረሱን ክለቡ አሳውቋል።
አስተያየት ይስጡ