የዋልያዎቹን መለያ መልበስን ስለሚፈልገው አራተኛው ተጫዋች እንንገራችሁ።

አራተኛው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወትን የሚፈለገው ደግሞ የመሐል ተከላካዩ ፍራንሲስ ቦላንዴ ነው። ከአውስትራሊያ ምድር የተገኘው እና በእናቱ የኢትዮጵያ ደም ያረፈበት ይህ አንድ ሜትር ከሰማንያ አምስት የሚረዝመው የመሐል ተከላካዩ እግር ኳስን በዛው አውስትራሊያ ሩፕታል ፣ ሊዮቤንዶርፍ እና ሆርን በተባሉ ወጣት ቡድኖች ውስጥ መጫወት ከቻለ በኋላ በመቀጥል በዛው በሀገሪቷ ለሚገኙት ኤስ ቪ ሆርን ፤ ማወር ወርክ ፣ ኤስ ሲ ኒውስ ዴል እና ማርቸስ ፊልድ ግልጋሎት በመስጠት ጥሩ ቆይታን አድርጎ በመቀጠል ወደ አሜሪካን በማምራትም አሽቬሊ ሲቲ እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርሲቲ በሚተዳደረው ኬይስ ሰር ተብሎ ለሚጠራ ቡድን እየተጫወተ ይገኛል።
ይህም ተጫዋች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ለማገልገል ዝግጁ ስለ መሆኑ ይገልፃል።
አስተያየት ይስጡ