መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ ተከታታይ ድላቸዉን አስመዝግበዋል !
ሲዳማ ቡናቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ ተከታታይ ድላቸዉን አስመዝግበዋል !

አጋራ
አጋራ

 

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር የሶስተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ሁለተኛ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን 5ለ1 በሆነ ዉጤት አሸንፏል።

በቅርቡ ህይወታቸው ላለፈዉ ታላቁ የስፖርት ሰዉ ፍቅሩ ኪዳኔ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ በጀመረው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ማሳካት የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች ጥንቃቄ የተሞላበትን የጨዋታ ሂደት ሲከተሉ ሲስተዋል በተቃራኒው ፈረሰኞቹ በተሻለ የኳስ ቁጥጥር እና በመስመር ላይ በሚገኙ ኳሶች ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ በዚህም በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃ ላይ ግብ ማስቆጠር ችለዋል።

በዚህም በ10ኛዉ ደቂቃ ላይ የተገኘዉን ቅታት ምት በረከት ወልዴ በቀጥታ ወደ ግብነት ቀይሮ ፈረሰኞቹን መሪ ማድረግ ችሏል። ከግቧ መቆጠር በኋላ የጨዋታውን ሂደት በይበልጥ የተቆጣጠሩት ፈረሰኞቹ በ17ኛዉ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ግብ አስቆጥረዋል። በዚህም ሰለሞን ሀብቴ ቢኒያም በላይ ላይ የሰራዉን ጥፋት ተከትሎ የተገኘዉን ፍፁም ቅጣት ምት ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ ማስቆጠር ችሏል።

ገና በጨዋታው የመጀመሪያዉ ደቂቃ ላይ ሁለት ግቦችን ያስተናገዱት ሲዳማዎች በጥቂቱም ቢሆን ወደ ጨዋታዉ ተመልሰዉ ጥሩ የግ ዕድሎችን መፍጠር ችለዋል። በ33ኛዉ ደቂቃ ላይም ምኞት ደበበ ይገዙ ላይ በሰራዉ ጥፋት የተገኘዉን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ ይገዙ አስቆጥሮ ክለቡን ወደ ጨዋታዉ አስችሏል።

ነገር ግን ፈረሰኞቹ በድጋሚ በአጋማሹ ላይ ሶስተኛ ግብ ማስቆጠር ችለዋል በዚህም አማካዩ ዳዊት ተፈራ ያቀበለዉን ኳስ ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ ወደ ግብነት ቀይሮ የክለቡን የግብ መጠን ወደ ሶስት ከፍ ማድረግ ሲችል ፤ በድጋሚ አጥቂዉ የተገኘዉን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት ቀይሮ በአጋማሹ ሀትሪክ መስራት ችሏል።

ከዕረፍት መልስ የተረጋጋ የጨዋታ መንገድን በመከተል ያለ ምንም ስጋት ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ሲደርሱ የነበሩት ፈረሰኞቹ በ65ኛዉ ደቂቃ ላይ አምስተኛ ግባቸዉን አስቆጥረዋል። በዚህም ከግራ መስመር በኩል ያሻገረለትን ኳስ አማኑኤል ገ/ሚካኤል በማስቆጠር የክለቡን የግብ መጠን ወደ አምስት ከፍ ማድረግ ችሏል። በዚህም የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በፈረሰኞቹ 5ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...