ሰበታ ከተማን ሊይዝ ነው ተብሎ በከፍተኛ ሁኔታ ሲወራበት የነበረው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ መሆኑ ተረጋግጧል::
አሰልጣኙ በትላንትናው ዕለት ፌዴሬሽን ጽ/ቤት በመገኘት የሀዲያ ሆሳዕና አሠልጣኝ መሆኑን በፊርማው በማረጋገጥ ሲራገብ የነበረው ወሬ ብቻ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ይህም የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ አሰልጣኙ የትም አይሄድም ያሉትን አቋማቸውን ያሳየ ሆኗል፡፡
አስተያየት ይስጡ