የአምስቱ የኮቪድ 19 ተጠቂ ተጨዋቾች ውጤት ዛሬ ይታወቃል…

የአምስቱ የኮቪድ 19 ተጠቂ
ተጨዋቾች ውጤት ዛሬ ይታወቃል…

*… ዋሊያዎቹ ተደናግጠዋል…..

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሰጠው ማሳሰቢያ
ከነበሩበት ሆሊዴይ ሆቴል ወጥተው ዋሊያዎቹ ወዳሉበት ካፍ አካዳሚ የተመለሱት 5ቱ የኮቪድ 19 ተጠቂ ተጨዋቾች ትላንት በድጋሚ መመርመራቸው ታውቋል፡፡

ተጨዋቾቹ ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆናቸው ሳይታወቅ ወደ አካዳሚው እንዲመጡ ሲደረግ ነጻ የሆኑት ተጨዋቾች መደንገጣቸው ታውቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ተጨዋቾቹን ለማስመርመር ገስት ሀውስ የፈለገ ቢሆንም አካዳሚው የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ሌሎቹ ተጨዋቾችን ሳይጠጉ ራቅ ባለ ክፍል ውስጥ እንዲያርፉ አድርጓል፡፡ ያም ቢሆን ታዲያ ነጻ የሆኑት ቀሪዎቹ ተጨዋቾች ፍርሃት እንደተሰማቸው መረጃውን ከተጨዋቾቹ አግኝቻለሁ፡፡
በአሁኑ ወቅት አምስቱ ተጨዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የድጋሚ ምርመራ ውጤታቸው ነጻ መሆናቸውን ካሳየ ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሚኖረው የልምምድ ሰአት ላይ ቡድኑን ተቀላቅለው በግላቸው ልምምድ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport