ፈረሰኞቹን በምክትል አሰልጣኝነት ሲመራ የነበረው አሰልጣኘ ደረጄ ተስፋዬ /አንገቴ/ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መለያየቱ ተሰማ።
አሰልጣኝ ደረጄ ከ8 አመት በላይ የክለቡ ቆይታው ከ17 አመትና ከ20 አመት በታች ቡድኖችን በዋና አሰልጣኝነት ዋናውን ቡድን ደግሞ በምክትልና በዋና አሰልጣኝነት መርቷል።
አምና በነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየርር ሊግ አብዛኛው ጨዋታን በምክትልነት ከሰራ በኋ የመጨረሻዎቹን የሊግ ግጥሚያዎች ፈረሰኞችን በዋና አሰልጣኝነት መርቷል። አሰልጣኙ ከሰምኑ በግል ምክንያት መቀጠል እንደማይችል በመግለጽ
ከስራው ለመልቀቅ ያቀበው ጥያቄ በክለቡ አመራሮች ተቀባይነት አግኝቶ መለያየታቸው ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል።