መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና ሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ ወደ ሀዋሳ እንዲመለስ አዘዘ
ሲዳማ ቡና

ሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ ወደ ሀዋሳ እንዲመለስ አዘዘ

አጋራ
አጋራ

 

በፕሪሚየር ሊጉ ጅማሮ ውጤታማ መሆን ያልቻለው ሲዳማ ቡና አሰልጣኙን ወንድማገኝ ተሾመን ከባህርዳር ወደ ሀዋሳ እንዲመለስ ማዘዙ ተሰማ።

ከውስጥ አዋቂ በተገኘ መረጃ ሲዳማ ቡናዎች ከድሬዳዋ ከተማ 2ለ2 ተለያይተው በሀድያ ሆሳዕና 4ለ1 በፈረሰኞቹ 5ለ1 ተረትተው 11 ግብ ተቆጥሮባቸው 4 ግብ ብቻ አስቆጥረው ማግኘት ካለባቸው 9 ነጥብ 1 ነጥብ ብቻ ማሳካታቸው በዝውውሩ በከፍተኛ ሁኔታ ለተሳተፉት የሲዳማ ቡና አመራሮች የሚዋጥ አልሆነም።

ክለቡ አሰልጣኙና ቡድን መሪውን ወደሀዋሳ እንዲመለሱ ከማዘዙ ውጪ ጥሪው ለስንብት ይሁን ለምክክር አልታወቀም በቀጣዩ ሀሙስ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ሲጫወቱ አሰልጣኙ ወንድማገኝ ይሁን አዲስ አሰልጣኝ የታወቀ ነገርም የለም
የሲዳማ ቡና ቦርድም ለነገ 8 ሰዓት ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል።

በፕሪሚየር ሊጉ ቀጣይ ጨዋታዎች የሚሰናበቱና የሚተኩ አሰልጣኞች እነማን ይሆኑ? የሚለው የብዙሃኑን የስፖርት ቤተሰብ ትኩረት የሳበ ሆኗል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ በዛሬው ጨዋታ አይሰለፍም

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የግብ ዘብ ከዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ውጪ ሆኗል። በትላንትናው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ ታገደ

ዩጋንዳዊው የሲዳማ ቡና የግብ ዘብ ከማንኛውም እግር ኳስ ታግዷል። በዩጋንዳ ፕሪምየር ሊግ...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ሲዳማ ቡና ከአበባየው ሀጂሶ ጋር ተለያየ

አማካዩ ቀሪ ውል እየቀረው ሲዳማ ቡናን ለቋል። ሁለት ወሳኝ ዝውውሮችን የፈፀመው የአሰልጣኝ...