By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ባህርዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር አቻ ሲለያዩ ፤ ሲዳማ ቡናም ወደ አሸናፊነት መመለስ የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ዜናዎችሀዋሳ ከተማድሬዳዋ ከተማባህርዳር ከተማሲዳማ ቡናየጨዋታ ዘገባየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ባህርዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር አቻ ሲለያዩ ፤ ሲዳማ ቡናም ወደ አሸናፊነት መመለስ የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንታት ዕድሜ ብቻ በቀረዉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ነኛ ሳምንት የመክፈቻ ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር መርሐግብራቸዉን አንድ አቻ በሆነ ዉጤት አገባደዋል።

ቀን ዘጠኝ ሰዓት ሲል በዋና ዳኛ ቢኒያም ወርቅአገኘሁ ፊሽካ በጀመረዉ የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ተመጣጣኝ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን እያስመለከቱን ጅማሮ ቢያደርጉም ፤ ገና በጊዜ ግን ማለትም በአስረኛዉ ደቂቃ ላይ የጣና ሞገዶቹ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል ። በዚህም በተጠቀሰዉ ደቂቃ የአብስራ ተስፋየ ወደ ሳጥን ያሻገራትን ኳስ የሀዋሳዉ ተከላካይ ሰለሞን ወዴሳ ኳሷን በዕጅ መንካቱን ተከትሎ የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት አምበሉ ፍቅረሚካኤል አለሙ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል።

ከግቧ መቆጠር በኋላ በተደጋጋሚ በፊት መስመር ተጫዋቾቹ የመስመር ላይ ማጥቃት አደጋ ለመፍጠር ይጥሩ የነበሩት ባህርዳር ከተማዎች በፍራኦል መንግስቱ እና ፍቅረሚካኤል አማካኝነት የተወሰኑ አጋጣሚዎችን ቢያገኙም ነገር ግን መጠቀም ሳይችሉ ሲቀሩ ፤ ገና በጊዜ ግብ የተቆጠረባቸዉ ሀይቆቹም በመልሶ ማጥቃት የአቻነት ግብ ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ከዕረፍት በፊት ሳይሳካ ቀርቶ አጋማሹ በባህርዳር መሪነት ተጠናቋል።

- ማሰታውቂያ -

ከዕረፍት መልስ እዮብ አለማየሁን እና ቸርነት አውሽን በሌሎች ተጫዋቾች ቀይረዉ በማስወጣት የማጥቃት ቅርፃቸዉን ለመቀየር ጥረት ያደረጉት ሀዋሳ ከተማዎች ምንም እንኳን በእንቅስቃሴ ረገድ የተለየ ነገር ማስመልከት ባይችሉም ከብዙ ጥረት በኋላ በ79ነኛዉ ደቂቃ ላይ በአጥቂዉ አሊ ሱለይማን የፍፁም ቅጣት ምት ግብ አማካኝነት የአቻነት ግብ አስቆጥረዉ መርሐግብራቸዉን አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ፈፅመዋል።

በዕለቱ ሁለተኛ መርሐግብር ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማን ሁለት ለዜሮ በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

በዋና ዳኛ ሚካኤል ጣዕመ መሪነት አመሻሽ 12:00 ሰዓት በጀመረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ገና በጊዜ ሲዳማ ቡናዎች ጨዋታዉን መምራት የጀመሩበትን ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም በአምስተኛዉ ደቂቃ ላይ ከወደ ግራ መስመር በኩል ከቅጣት ምት የተሻማዉ ኳስ የግቡን ቋሚ ገጭቶ ሲመለስ ኳሱን ያገኘው ኢማኑኤል ላሪየ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን ሲዳማ ቡና መሪ ማድረግ ችሏል።

ከዚች ግብ መቆጠር ከአራት ደቂቃዎች በኋላ በ9ነኛዉ ደቂቃ ላይ ደግሞ ቶሎ ቶሎ ወደ ድሬዳዋ የግብ ክልል መድረስ የቻሉት ሲዳማ ቡናዎች በድጋሚ ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር ችለዋል። በዚህም ከቀኝ በኩል የተገኘዉን የቅጣት ምት ኳስ የሲዳማዉ አምበል ደስታ ደሙ በቀጥታ ወደ ግብነት ቀይሮ መሪነታቸዉን ወደ ሁለት ለዜሮ ከፍ ማድረግ ችለዋል።

ገና በጊዜ ተከታታይ ጎሎች የተቆጠሩባቸዉ ድሬዳዋ ከተማዎች ወደ ጨዋታዉ ለመግባት በኳስ ቁጥጥሩ ተሽለዉ ሲንቀሳቀሱ የተመለከትናቸው ቢሆንም ነገር ግን የሚገኙ ዕድሎችን ወደ ግብነት በመቀየርም ሆነ ስል በመሆን ረገድ ግን ደካማ ሁነዉ ተስተዉሏል። በተቃራኒው ጨዋታዉን በመምራት ላይ የነበሩት ሲዳማ ቡናዎች በቀሪ የጨዋታዉ ደቂቃዎች በተደጋጋሚ ድንቅ የሚባሉ ዕድሎችን አግኝተዉ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በመጠቀሙ ረገድ እየተዳከሙ ቀጥለዋል። ይህንን ተከትሎም ሁለቱም ክለቦች ተጨማሪ ግብም ሆነ የአቻነት ግብ ለማግኘት ያደረጉት ጥረት ፍሬ ሳያፈራ ቀርቶ መርሐግብሩ ጥሩ በነበረዉ በሲዳማ ቡና ሁለት ለዜሮ አሸናፊነት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ስምንተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ! እና 29ኛ ሳምንት የፕሮግራም ለውጥ
Next Article በዕለቱ በተደረገዉ ብቸኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ሀድያ ሆሳዕናን ማሸነፍ ችሏል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ወላይታ ድቻዜናዎች

ወላይታ ድቻ ገብረክርስቶስ ቢራራን በአሰልጣኝነት ሾመ

ዳዊት ብርሀነ By ዳዊት ብርሀነ 7 years ago
​የደቡብ ክልል ካስትል ዋንጫ የምድብ ለ ጨዋታዎች / livescore
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ
ሃይላንድ ውሃና ፈረሰኞቹ ተጣመሩ
ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ | ቀጥታ የውጤት መግለጫ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?